እንዲሁም ካህኑ ኬልቅያስና አኪቃም ዓክቦርም ሳፋንና ዓሳያም ወደ ልብስ ጠባቂው ወደ ሓስራ ልጅ ወደ ቴቁዋ ልጅ ወደ ሴሌም ሚስት ወደ ነቢዪቱ ወደ ሕልዳና ሄዱ፤ እርስዋም በዚያ በኢየሩሳሌም በሁለተኛው ክፍል ተቀምጣ ነበር፤ ለእርስዋም ነገሩአት።
ኢሳይያስ 8:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ነቢዪቱም ቀረብሁ፤ እርስዋም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች። እግዚአብሔርም አለኝ፥ “ስሙን ‘ቸኩለህ ማርክ፤ ፈጥነህም በዝብዝ’ ብለህ ጥራው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔም ወደ ነቢዪቱ ሄድሁ፤ እርሷም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች። እግዚአብሔርም፣ እንዲህ አለኝ፤ “ስሙን ማኸር-ሻላል-ሃሽ-ባዝ ብለህ ጥራው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም ወደ ነቢዪቱ ሄድሁ፤ እርሷም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች። ጌታም፤ እንዲህ አለኝ፦ “ስሙን ማኸር-ሻላል-ሃሽባዝ ብለህ ጥራው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከጥቂት ጊዜ በኋላ ከነቢይቱ ሚስቴ ጋር ተገናኘሁ፤ እርስዋም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች፤ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “ስሙን ‘ለማጥፋትና ለምርኮ ፍጠን!’ ብለህ ጥራው መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ነቢይቱም ቀረብሁ፥ እርስዋም ፀነሰች፥ ወንድ ልጅንም ወለደች። |
እንዲሁም ካህኑ ኬልቅያስና አኪቃም ዓክቦርም ሳፋንና ዓሳያም ወደ ልብስ ጠባቂው ወደ ሓስራ ልጅ ወደ ቴቁዋ ልጅ ወደ ሴሌም ሚስት ወደ ነቢዪቱ ወደ ሕልዳና ሄዱ፤ እርስዋም በዚያ በኢየሩሳሌም በሁለተኛው ክፍል ተቀምጣ ነበር፤ ለእርስዋም ነገሩአት።
በነጋውም ጳስኮር ኤርምያስን ከአዘቅት ውስጥ አወጣው። ኤርምያስም እንዲህ አለው፥ “እግዚአብሔር ስምህን፦ ዘዋሪ ስደተኛ እንጂ ጳስኮር ብሎ አይጠራህም።