ኢሳይያስ 48:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም አሁን እንጂ ከጥንት አልተፈጠሩም፤ አንተም፥ “እነሆ፥ ዐውቄአቸዋለሁ” እንዳትል ከዛሬ በፊት አልሰማሃቸውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም የተፈጠሩት አሁን እንጂ ጥንት አይደለም፤ ስለ እነርሱም ከዛሬ በፊት አልሰማህም። ስለዚህ፣ ‘አዎን፤ ስለ እነርሱ ዐውቃለሁ’ ማለት አትችልም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም አሁን እንጂ ከጥንት አልተፈጠሩም፤ አንተም፦ “እነሆ፥ አስቀድሜ አውቄአቸዋለሁ” እንዳትል ከዛሬ በፊት አልሰማሃቸውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ ከብዙ ጊዜ በፊት ሳይሆን አሁን የተፈጠሩ ናቸው፤ እናንተም ‘ቀደም ብለን ዐውቀናቸዋል’ እንዳትሉ ከአሁን በፊት ከቶ አልሰማችኋቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም አሁን እንጂ ከጥንት አልተፈጠሩም፥ አንተም፦ እነሆ፥ አውቄአቸዋለሁ እንዳትል ከዛሬ በፊት አልሰማሃቸውም። |
አላወቅህም፤ አላስተዋልህም፤ ጆሮህን ከጥንት አልከፈትሁልህም፤ አንተ ፈጽሞ ወንጀለኛ እንደ ሆንህ፥ ከማኅፀንም ጀምረህ ተላላፊ ተብለህ እንደ ተጠራህ ዐውቄአለሁና።
ታዳጊህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ሕይወቱን የሚያስጨንቃትን፥ በአሕዛብ የተጠላውን የአለቆችን ባርያ ቀድሱት፤ ነገሥታት ያዩታል፤ አለቆችም ስለ እግዚአብሔር ብለው ተነሥተው ይሰግዱለታል፤ የእስራኤል ቅዱስ ታማኝ ነውና፥ እኔም መርጨሃለሁና።”