ኢሳይያስ 41:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያሳድዳቸዋልም፤ እግሮቹም በሰላም መንገድ ይሄዳሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሳደዳቸው፤ በሰላም ዐልፎ ሄደ፤ እግሩም ቀድሞ ባልረገጠው መንገድ ተጓዘ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሳደዳቸው፥ እግሮቹም አስቀድመው ባልሄዱባት ሰላማዊ መንገድ አለፈ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በፊት እግሮቹ ሄደውበት በማያውቁት መንገድ እነርሱን በፍጥነት ሲያሳድድ ምንም ጒዳት አይደርስበትም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሳደዳቸው፥ እግሮቹም አስቀድመው ባልሄዱባት መንገድ በደኅንነት አለፈ። |
ከምሥራቅ ጽድቅን ያስነሣ፥ ይከተለውም ዘንድ ወደ እግሩ የጠራው ማን ነው? በአሕዛብና በነገሥታት ፊት ድንጋጤን ያመጣል። ጦሮቻቸውን በምድር ያስጥላቸዋል፤ ቀስቶቻቸውም እንደ ገለባ ይረግፋሉ።