ኢሳይያስ 40:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ውኆችን በእፍኙ የሰፈረ፥ ሰማይንም በስንዝሩ የለካ፥ ምድርንም ሁሉ ሰብስቦ በእጁ የያዘ፥ ተራሮችን በሚዛን፥ ኮረብቶችንም በሚዛኖች የመዘነ ማን ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ውሆችን በዕፍኙ የሰፈረ፣ ሰማያትን በስንዝሩ የለካ፣ የምድርን ዐፈር በመስፈሪያ ሰብስቦ የያዘ፣ ተራሮችን በሚዛን፣ ኰረብቶችንም በመድሎት የመዘነ ማነው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ውኆችን በእፍኙ የሰፈረ፥ ሰማይንም በስንዝር የለካ፥ የምድርንም አፈር በመስፈሪያ ሰብስቦ የያዘ፥ ተራሮችን በሚዛን ኮረብቶችንም በሚዛኖች የመዘነ ማን ነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ውቅያኖስን በእፍኙ፥ ሰማይንም በስንዝሩ፥ የምድርን ዐፈር በቊና መለካት የሚችል ማን ነው? ተራራዎችንና ኰረብቶችንስ በሚዛን የሚመዝን ማን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ውኆችን በእፍኙ የሰፈረ፥ ሰማይንም በስንዝር የለካ፥ የምድርንም አፈር በመስፈሪያ ሰብስቦ የያዘ፥ ተራሮችን በሚዛን ኮረብቶችንም በሚዛኖች የመዘነ ማን ነው? |
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ሰማይ እጅግ ከፍ ቢል፥ የምድርም መሠረት ፈጽሞ ዝቅ ቢል በዚያ ጊዜ ስላደረጉት ነገር ሁሉ፥ የእስራኤልን ዘር ሁሉ እንቃለሁ ይላል እግዚአብሔር።
እነሆ ነጐድጓድን የሚያጸና፥ ነፋስንም የፈጠረ፥ የመሢሕን ነገር ለሰው የሚነግር፥ ንጋትን ጭጋግ የሚያደርግ፥ በምድርም ከፍታዎች ላይ የሚረግጥ፥ ስሙ ሁሉን የሚችል ጌታ እግዚአብሔር እኔ ነኝ።”