Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤርምያስ 31:37 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

37 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሰማይ እጅግ ከፍ ቢል፥ የም​ድ​ርም መሠ​ረት ፈጽሞ ዝቅ ቢል በዚያ ጊዜ ስላ​ደ​ረ​ጉት ነገር ሁሉ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ዘር ሁሉ እን​ቃ​ለሁ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

37 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በላይ ያሉትን ሰማያትን መለካት፣ በታችም ያሉትን የምድር መሠረቶች መመርመር ከተቻለ፣ በዚያ ጊዜ የእስራኤልን ዘር ሁሉ፣ ስላደረጉት ነገር ሁሉ እጥላቸዋለሁ፤” ይላል እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

37 ጌታ እንዲህ ይላል፦ በላይ ያለው ሰማይ ቢለካ፥ በታችም ያለው የምድር መሠረት ቢመረመር፥ በዚያን ጊዜ ስላደረጉት ነገር ሁሉ የእስራኤልን ትውልድ በሙሉ እጥላለሁ፥ ይላል ጌታ።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

37 እግዚአብሔር ሕዝቡን እስራኤልን በሠሩት በደል ምክንያት ይጥላቸዋል ማለት የሚቻለው የሰማይ ስፋቱ ተለክቶ፥ የምድርም መሠረቶች ሁሉ ተመርምረው ለመታወቅ ቢችሉ ብቻ ነው። እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

37 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሰማይ በላይ ቢከነዳ፥ የምድርም መሠረት በታች ቢመረመር፥ በዚያን ጊዜ ስላደረጉት ነገር ሁሉ የእስራኤልን ዘር ሁሉ እጥላለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 31:37
13 Referencias Cruzadas  

ውኆ​ችን በእ​ፍኙ የሰ​ፈረ፥ ሰማ​ይ​ንም በስ​ን​ዝሩ የለካ፥ ምድ​ር​ንም ሁሉ ሰብ​ስቦ በእጁ የያዘ፥ ተራ​ሮ​ችን በሚ​ዛን፥ ኮረ​ብ​ቶ​ች​ንም በሚ​ዛ​ኖች የመ​ዘነ ማን ነው?


የሰ​ማ​ይን ሠራ​ዊት መቍ​ጠር፥ የባ​ሕ​ር​ንም አሸዋ መስ​ፈር እን​ደ​ማ​ይ​ቻል፥ እን​ዲሁ የባ​ሪ​ያ​ዬን የዳ​ዊ​ትን ዘርና የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​ኝን ሌዋ​ው​ያ​ንን አበ​ዛ​ለሁ።”


አንተ ባሪ​ያዬ ያዕ​ቆብ ሆይ! እኔ ከአ​ንተ ጋር ነኝና አት​ፍራ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ አን​ተ​ንም ያሳ​ደ​ድ​ሁ​ባ​ቸ​ውን አሕ​ዛ​ብን ሁሉ ፈጽሜ አጠ​ፋ​ለ​ሁና፥ አን​ተን ግን ፈጽሜ አላ​ጠ​ፋ​ህም፤ በመ​ጠን እቀ​ጣ​ሃ​ለሁ፥ ያለ ቅጣ​ትም አል​ተ​ው​ህም።”


ተራ​ሮች ሳይ​ወ​ለዱ፥ ምድ​ርም ዓለ​ምም ሳይ​ሠሩ፥ ከዘ​ለ​ዓ​ለም እስከ ዘለ​ዓ​ለም ድረስ መቼም መች አንተ ነህ።


አድ​ንህ ዘንድ ከአ​ንተ ጋር ነኝና፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ አን​ተ​ንም የበ​ተ​ን​ሁ​ባ​ቸ​ውን አሕ​ዛ​ብን ሁሉ ፈጽሜ አጠ​ፋ​ለሁ፤ አን​ተን ግን ፈጽሜ አላ​ጠ​ፋ​ህም፤ በመ​ጠን እቀ​ጣ​ሃ​ለሁ፥” ያለ ቅጣ​ትም ከቶ አል​ተ​ው​ህም።”


የያ​ዕ​ቆ​ብን ዘርና የይ​ሁ​ዳን ዘር አመ​ጣ​ለሁ፤ የተ​ቀ​ደ​ሰው ተራ​ራ​ዬ​ንም ይወ​ር​ሳሉ፤ እኔ የመ​ረ​ጥ​ኋ​ቸ​ውና ባሪ​ያ​ዎ​ችም ይወ​ር​ሱ​አ​ታል፤ በዚ​ያም ይኖ​ራሉ።


ከሰ​ማይ በታች ያለ የም​ድ​ር​ንስ ስፋት አስ​ተ​ው​ለ​ሃ​ልን? መጠ​ኑም ምን ያህል እንደ ሆነ እስኪ ንገ​ረኝ!


ከኖኅ ዘመን ውኃ ጀምሮ ይህ ለእኔ ምስ​ክር ነው፤ ቀድሞ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ምድ​ርን እን​ዳ​ል​ቈ​ጣት እንደ ማልሁ፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios