የኬልቅዩም ልጅ ኤልያቄም ሳምናስም ዮአስም ራፋስቂስን፥ “እኛ እንሰማለንና በሱርስት ቋንቋ ለአገልጋዮችህ ተናገር፤ በዕብራይስጥም ቋንቋ አትናገረን፤ በቅጥርም ላይ ያለው ሕዝብ በሚሰማው ቋንቋ ለምን ትናገራለህ?” አሉት።
ኢሳይያስ 36:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም ዝም አሉ፤ አንዳችም አልመለሱለትም፤ ንጉሡ እንዳይመልሱለት አዝዞ ነበርና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ሕዝቡ ዝም አለ፤ ምንም መልስ አልሰጠም፤ ንጉሡ፣ “መልስ እንዳትሰጡ” ሲል አዝዞ ነበርና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱ ግን ዝም አሉ፥ ንጉሡ እንዳይመልሱለት አዝዞ ነበርና “አንዳችም አልመለሱለትም”። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቡም ቀደም ሲል ንጉሥ ሕዝቅያስ ባዘዛቸው መሠረት አንዲት ቃል ሳይናገሩ ዝም አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም ዝም አሉ፥ አንዳችም አልመለሱለትም፥ ንጉሡ እንዳይመልሱለት አዝዞ ነበርና። |
የኬልቅዩም ልጅ ኤልያቄም ሳምናስም ዮአስም ራፋስቂስን፥ “እኛ እንሰማለንና በሱርስት ቋንቋ ለአገልጋዮችህ ተናገር፤ በዕብራይስጥም ቋንቋ አትናገረን፤ በቅጥርም ላይ ያለው ሕዝብ በሚሰማው ቋንቋ ለምን ትናገራለህ?” አሉት።
የቤቱ አዛዥ የኬልቅዩ ልጅ ኤልያቄም፥ ጸሓፊው ሳምናስ፥ ታሪክ ጸሓፊውም የአሳፍ ልጅ ዮአስ ልብሳቸውን ቀድደው ወደ ሕዝቅያስ ገቡ፥ የራፋስቂስንም ቃል ነገሩት።