ቅጥሩን እንዲያፈርሱ ከተማዪቱንም እንዲወስዱ፥ በቅጥር ላይ የተቀመጡትን የኢየሩሳሌምን ሕዝብ ያስፈራቸውና ያስደነግጣቸው ዘንድ በታላቅ ድምፅ በዕብራይስጥ ቋንቋ ይጮኽባቸው ነበር።
ኢሳይያስ 36:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ራፋስቂስም ቆሞ በታላቅ ድምፅ በዕብራይስጥ እንዲህ ብሎ ጮኸ፥ “የታላቁን የአሦርን ንጉሥ ቃል ስሙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጦር አዛዡም ቆሞ በዕብራይስጥ ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፤ “የታላቁን ንጉሥ፣ የአሦርን ንጉሥ ቃል ስሙ! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ራፋስቂስም ቆሞ በታላቅ ድምፅ በአይሁድ ቋንቋ እንዲህ ብሎ ጮኸ፦ “የታላቁን የአሦርን ንጉሥ ቃል ስሙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ የአሦር ባለ ሥልጣን ከተቀመጠበት ተነሥቶ ቆመ፤ ድምፁንም ከፍ አድርጎ በዕብራይስጥ ቋንቋ እንዲህ እያለ መናገር ጀመረ፦ “የታላቁን የአሦር ንጉሥ ቃል ስሙ! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ራፋስቂስም ቆሞ በታላቅ ድምፅ በአይሁድ ቋንቋ እንዲህ ብሎ ጮኸ፦ የታላቁን የአሦርን ንጉሥ ቃል ስሙ። |
ቅጥሩን እንዲያፈርሱ ከተማዪቱንም እንዲወስዱ፥ በቅጥር ላይ የተቀመጡትን የኢየሩሳሌምን ሕዝብ ያስፈራቸውና ያስደነግጣቸው ዘንድ በታላቅ ድምፅ በዕብራይስጥ ቋንቋ ይጮኽባቸው ነበር።
ኤልያቄምና ሳምናስ፥ ዮአስም ራፋስቂስን፥ “እኛ እንሰማለንና እባክህ፥ በሶርያ ቋንቋ ለባሪያዎችህ ተናገር፤ በቅጥርም ላይ ባለው ሕዝብ ጆሮ በዕብራይስጥ አትናገረን” አሉት።
ራፋስቂስ ግን፥ “ጌታዬ ይህን ቃል እናገር ዘንድ ወደ እናንተና ወደ ጌታችሁ ልኮኛልን? ከእናንተ ጋር ኵሳቸውን ይበሉ ዘንድ፥ ሽንታቸውንም ይጠጡ ዘንድ በቅጥር ላይ ለተቀመጡት ሰዎች እነግራቸው ዘንድ አይደለምን?” አላቸው።
ራፋስቂስም አላቸው፥ “ለሕዝቅያስ እንዲህ ብላችሁ ንገሩት፦ ታላቁ የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ በማን ትተማመናለህ?
ምናልባት በሕያው አምላክ ላይ ይገዳደር ዘንድ ጌታው የአሦር ንጉሥ የላከውን የራፋስቂስን ቃል አምላክህ እግዚአብሔር ይሰማ እንደ ሆነ፥ አምላክህ እግዚአብሔርም ስለ ሰማው ቃል ይገሥጸው እንደ ሆነ፥ ስለዚህ ለቀረው ቅሬታ ጸልይ” አሉት።
ስለዚህ፥ እነሆ፥ እግዚአብሔር ብርቱና ብዙ የሆነውን የወንዝ ውኃ፥ የአሦርን ንጉሥና ክብሩን ሁሉ ያመጣባቸዋል፤ ወንዙም ሞልቶ ይወጣል፤ በዳሮቻቸውም ሁሉ ላይ ይፈስሳል፤