በዚያ ቀን ድምፁን ከፍ አድርጎ፥ “እኔ በቤቴ ውስጥ እንጀራ ወይም ልብስ የለኝምና ለሕዝቡ አለቃ አልሆንም” ብሎ መለሰለት።
ኢሳይያስ 3:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰውም በአባቱ ቤተ ሰብእ ውስጥ ወንድሙን ይዞ፥ “አንተ ልብስ አለህ፥ አለቃም ሁንልን፥ ምግባችንም ከእጅህ በታች ትሁን” ቢለው፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰውም በአባቱ ቤት ከወንድሞቹ አንዱን ይዞ፣ “አንተ ልብስ ስላለህ መሪ ሁነን፤ ይህንም የፍርስራሽ ክምር ግዛ!” ይለዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰውም በአባቱ ቤት ከወንድሞቹ አንዱን ይዞ፤ “አንተ ልብስ ስላለህ መሪ ሁነን፤ ይህንንም የፍርስራሽ ክምር ግዛ” ይለዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቤተሰብ አባላት በአባታቸው ቤት አንዱን ወንድማቸውን መርጠው “አንተ ሌላው ቢቀር እንኳ የምትለብሰው ልብስ አለህ፤ ስለዚህ እባክህ አለቃችን ሁን፤ ፍርስራሽ ሁሉ በአንተ ሥልጣን ሥር ይሁን” ይሉታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰውም በአባቱ ቤት ውስጥ ወንድሙን ይዞ፦ አንተ ልብስ አለህ አለቃም ሁንልን ይህችም ባድማ ከእጅህ በታች ትሁን ሲለው፥ |
በዚያ ቀን ድምፁን ከፍ አድርጎ፥ “እኔ በቤቴ ውስጥ እንጀራ ወይም ልብስ የለኝምና ለሕዝቡ አለቃ አልሆንም” ብሎ መለሰለት።
በዚያም ቀን ሰባት ሴቶች፥ “የገዛ እንጀራችንን እንበላለን፤ የገዛ ልብሳችንንም እንለብሳለን፤ ስምህ ብቻ በእኛ ላይ ይጠራ፤ መሰደባችንንም አርቅልን” ብለው አንዱን ወንድ ይይዙታል።