ኢሳይያስ 28:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሻውን ባስተካከለ ጊዜ ጥቂት ጥቍሩን አዝሙድ፥ ከሙኑንም፥ ዳግመኛም ስንዴውን፥ ገብሱንም፥ አጃውንም በየስፍራው የሚዘራ አይደለምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዕርሻውን አስተካክሎ፣ ጥቍር አዝሙድና ከሙን አይዘራምን? ስንዴውንስ በትልሙ፣ ገብሱን በተገቢ ቦታው፣ አጃውንም በተመደበው ስፍራ አይዘራምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሻውን አስተካክሎ ጥቁሩን አዝሙድ፥ ከሙኑንም፥ ስንዴውንም በተርታ፥ ገብሱንም በስፍራው፥ አጃውንም በደረጃው አይዘራምን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ጊዜ መሬቱን ካስተካከለ በኋላ ጥቊር አዝሙድና ከሙን፥ ስንዴና ገብስ እንዲሁም አጃ የመሳሰሉትን አዝርዕት በየምድቡ ይዘራ የለምን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጓሉንስ ይከሰክሳልን? እርሻውን ባስተካከለ ጊዜ ጥቁሩን አዝሙድ፥ ከሙኑንም፥ ስንዴውንም በተርታ፥ ገብሱንም በስፍራው፥ አጃውንም በደረጃው የሚዘራ አይደለምን? |
“አንተም ስንዴንና ገብስን፥ አተርንና ባቄላን፥ ምስርንና አጃን ወደ አንተ ውሰድ፤ በአንድ ዕቃም ውስጥ አድርገህ እንጀራ ጋግር፤ በጎንህ እንደ ተኛህባት ቀን ቍጥር ሦስት መቶ ዘጠና ቀን ትበላዋለህ።
“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! ከአዝሙድና ከእንስላል ከከሙንም አሥራት ስለምታወጡ፥ ፍርድንና ምሕረትን ታማኝነትንም፥ በሕግ ያለውን ዋና ነገር ስለምትተዉ፥ ወዮላችሁ፤ ሌላውን ሳትተዉ ይህን ልታደርጉ ይገባችሁ ነበር።