ኢሳይያስ 28:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መዋጋትን አንችልም፤ እናንተንም ለመሰብሰብ ደካሞች ነን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግር ዘርግቶ እንዳይተኛ ዐልጋው ዐጭር ነው፤ ሰውነትንም ለመሸፋፈን ብርድ ልብሱ ጠባብ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰው በእርሱ ላይ ተዘርግቶ ቢተኛ አልጋው አጭር ነው፤ ሰውም ሰውነቱን መሸፈን ቢወድድ መጎናጸፊያ ጠባብ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚከተለው ምሳሌ እንደ ተነገረበት ሰው ትሆናላችሁ፤ ይህም ሰው በጣም አጭር በሆነ ድንክ አልጋ ላይ ተኝቶ እግሩን መዘርጋት ተሣነው፤ ልብሱም ጠባብ ከመሆኑ የተነሣ ሰውነቱን በሙሉ መሸፈን አልቻለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰው በእርሱ ላይ ተዘርግቶ ቢተኛ አልጋው አጭር ነው፥ ሰውም ሰውነቱን መሸፈን ቢወድድ መጎናጸፊያ ጠባብ ነው። |
ሁላችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነናል፤ ጽድቃችንም ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ በኀጢአታችን ምክንያት እንደ ቅጠል ረግፈናል፤ እንዲሁም ነፋስ ጠራርጎ ወስዶናል።