ኢሳይያስ 10:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም ያለቀና የተቈረጠ ነገርን በዓለም ሁሉ በእውነት ይፈጽማል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ የወሰነውን ጥፋት በምድር ሁሉ ላይ ይፈጽማልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ የወሰነውን ጥፋት በምድር ሁሉ ላይ ያመጣል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አዎ! የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር በሀገሪቱ በሞላ ቊርጥ ውሳኔ የሰጠበትን የጥፋት ፍርድ ያመጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም ያለቀ የተቈረጠ ነገርን በምድር ሁሉ መካከል ይፈጽማል። |
አሁንም በምድር ሁሉ ላይ የሚያደርገውን ያለቀና የተቈረጠ ነገርን ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ ሰምቻለሁና እስራታችሁ እንዳይጸናባችሁ እናንተ ደስ አይበላችሁ።