ኢሳይያስ 10:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሰማርያና በጣዖቶችዋም እንዳደረግሁ፥ እንዲሁ በኢየሩሳሌምና በጣዖቶችዋ አደርጋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሰማርያና በጣዖቶቿ ያደረግሁትን፣ በኢየሩሳሌምና በተቀረጹ ምስሎቿስ እንዲሁ አላደርግምን?” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሰማርያና በጣዖቶቿ ያደረግሁትን፤ በኢየሩሳሌምና በተቀረጹ ምስሎቿስ እንዲሁ አላደርግምን?” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሰማርያና በጣዖቶችዋ ላይ እንዳደረግሁት በኢየሩሳሌምና እዚያ በሚሰግዱላቸው ምስሎች ላይ አላደርገውምን?” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሰማርያና በጣዖቶችዋም እንዳደረግሁ፥ እንዲሁስ በኢየሩሳሌምና በጣዖቶችዋ አላደርግምን? |
ሕዝቅያስም፦ እግዚአብሔር ያድነናል ብሎ አያታልላችሁ። በውኑ የአሕዛብ አማልክት ሀገሮቻቸውን ከአሦር ንጉሥ እጅ አድነዋቸዋልን?
አማልክቶቻቸውንም በእሳት አቃጥለዋል፤ የእንጨትና የድንጋይ የሰው እጅ ሥራም ነበሩ እንጂ አማልክት አልነበሩምና ስለዚህ አጥፍተዋቸዋል።
ታላቂቱም እኅትሽ ከሴቶች ልጆችዋ ጋር በስተ ግራሽ የምትቀመጥ ሰማርያ ናት፤ ታናሽቱም እኅትሽ ከሴቶች ልጆችዋ ጋር በሰተ ቀኝሽ የምትቀመጥ ሰዶም ናት።