በዚያች ምድር ከሚኖሩ ሰዎች ጋር ቃል ኪዳን እንዳታደርግ፥ እነርሱ አምላኮቻቸውን ተከትለው በአመነዘሩና በሠዉላቸው ጊዜ እንዳይጠሩህ፥ ከመሥዋዕታቸውም እንዳትበላ፥
ሆሴዕ 3:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ከእኔ ጋር ብዙ ወራት ተቀመጪ፤ አታመንዝሪም፤ ሌላ ሰውንም አታግቢ፤ እኔም ከአንቺ ጋር እኖራለሁ” አልኋት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔም፣ “ከእኔ ጋራ ብዙ ቀን ተቀመጪ፤ አታመንዝሪ ወይም ሌላ ሰው አትውደጂ፤ እኔም ከአንቺ ጋራ እኖራለሁ” ብዬ ነገርኋት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለእርሷም፦ “የእኔ ሆነሽ ለብዙ ወራት ተቀመጪ፥ አታመንዝሪም፥ ለሌላ ሰውም አትሁኚ፤ እኔም እንዲሁ እሆንልሻለሁ” አልኋት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሳታመነዝሪና ሰውነትሽን ለማንኛውም ወንድ ሳትሰጪ እኔን እየጠበቅሽ ለብዙ ጊዜ መቈየት አለብሽ፤ እኔም ለአንቺ እንዲሁ አደርግልሻለሁ” ብዬ ነገርኳት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእኔ ጋር ብዙ ወራት ተቀመጪ፥ አታመንዝሪም፥ ለሌላ ሰውም አትሁኚ፥ እኔም እንዲሁ እሆንልሻለሁ አልኋት። |
በዚያች ምድር ከሚኖሩ ሰዎች ጋር ቃል ኪዳን እንዳታደርግ፥ እነርሱ አምላኮቻቸውን ተከትለው በአመነዘሩና በሠዉላቸው ጊዜ እንዳይጠሩህ፥ ከመሥዋዕታቸውም እንዳትበላ፥
የተማረከችበትንም ልብስ ታወልቅላታለህ፤ በቤትህም ታስቀምጣታለህ፤ ስለ አባቷና ስለ እናቷ አንድ ወር ሙሉ ታለቅሳለች፤ ከዚያም በኋላ ትደርስባታለህ፤ ባልም ትሆናታለህ፤ እርስዋም ሚስት ትሆንልሃለች።