ሆሴዕ 13:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዐመፅህን ወንጀል ታገሥሁት፤ የኤፍሬም ኀጢአቱም ተከማችትዋል ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኤፍሬም በደል ተከማችቷል፤ ኀጢአቱም በመዝገብ ተይዟል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የኤፍሬም በደል ታስሮአል፥ ኃጢአቱም ተከማችቶአል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የእስራኤል ኃጢአትና በደል ተጽፎ ተከማችቶአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የኤፍሬም በደል ታስሮአል፥ ኃጢአቱም ተከማችቶአል። |
ነገር ግን ልቡናህን እንደ ማጽናትህ፥ ንስሓም እንደ አለመግባትህ መጠን የእግዚአብሔር እውነተና ፍርድ በሚገለጥበት ቀን መቅሠፍትን ለራስህ ታከማቻለህ።