ሆሴዕ 1:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢሥህልትንም ጡት ባስጣሏት ጊዜ፥ ደግሞ ፀነሰች፤ ወንድ ልጅንም ወለደች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጎሜር፣ ሎሩሃማን ጡት ካስጣለች በኋላ ሌላ ወንድ ልጅ ወለደች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሎሩሃማንም ጡት ባስጣለች ጊዜ ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጎሜር ሎሩሐማን ጡት ካስጣለች በኋላ እንደገና ፀንሳ ወንድ ልጅ ወለደች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሎሩሃማም ጡት ባስጣለች ጊዜ፥ ደግሞ ፀነሰች ወንድ ልጅንም ወለደች። |
ደግሞ ፀነሰች፤ ሴት ልጅንም ወለደች። እግዚአብሔርም፥ “መለየትን እለያቸዋለሁ እንጂ ይቅር እላቸው ዘንድ የእስራኤልን ቤት ከእንግዲህ ወዲህ አልምራቸውምና ስምዋን ኢሥህልት ብለህ ጥራት፤
ነገር ግን የይሁዳን ልጆች ይቅር እላቸዋለሁ፤ እኔ አምላካቸውም እግዚአብሔር አድናቸዋለሁ እንጂ በቀስት ወይም በሰይፍ፥ ወይም በጦር፥ ወይም በሠረገላ፥ ወይም በፈረሶች፥ ወይም በፈረሰኞች የማድናቸው አይደለም” አለው።