ሆሴዕ 1:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም ሄዶ የዴብላይምን ልጅ ጎሜርን አገባ፤ እርስዋም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅንም ወለደችለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ እርሱ የዴቤላይምን ሴት ልጅ ጎሜርን አገባ፤ እርሷም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደችለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ሄዶ የዴቤላይምን ልጅ ጎሜርን አገባ፤ እርሷም ፀነሰች ወንድ ልጅንም ወለደችለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ሆሴዕ ሄዶ የዲብላይምን ልጅ ጎሜርን አገባ፤ እርስዋም ፀንሳ ወንድ ልጅ ወለደችለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም ሄዶ የዴቤላይምን ልጅ ጎሜርን አገባ፥ እርስዋም ፀነሰች ወንድ ልጅንም ወለደችለት። |
ስማቸውም የታላቂቱ ሐላ የታናሽ እኅቷም ሐሊባ ነበረ፤ እኔም አገባኋቸው፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለዱ። ስማቸውም ሐላ ሰማርያ ናት፤ ሐሊባ ደግሞ ኢየሩሳሌም ናት።