ቤትን ሁሉ ሰው ይሠራዋልና፤ ለሁሉ ግን ሠሪው እግዚአብሔር ነው።
እያንዳንዱ ቤት የራሱ ሠሪ አለው፤ ነገር ግን ሁሉን የሠራ እግዚአብሔር ነው።
ለእያንዳንዱ ቤት ሠሪ አለው፤ ሁሉን የሠራ ግን እግዚአብሔር ነው።
በእርግጥ ለእያንዳንዱ ቤት ሠሪ አለው፤ ሁሉን ነገር የሠራ ግን እግዚአብሔር ነው።
እያንዳንዱ ቤት በአንድ ሰው ተዘጋጅቶአልና፥ ሁሉን ያዘጋጀ ግን እግዚአብሔር ነው።
በኋላ ዘመን ግን ሁሉን ወራሽ ባደረገው፥ ሁሉንም በፈጠረበት በልጁ ነገረን።
ነገር ግን የባለቤት ክብሩ ከቤቱ እንደሚበልጥ፥ ክብሩ ከሙሴ ክብር ይልቅ እጅግ ይበልጣል፤
ሙሴስ በኋላ ስለሚነገረው ነገር ምስክር ሊሆን በቤቱ ሁሉ እንደ ሎሌ የታመነ ነበረ።