ዕብራውያን 12:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህም የላሉትን እጆች፥ የሰለሉትንም ጕልበቶች አቅኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ የዛለውን ክንዳችሁንና የደከመውን ጕልበታችሁን አበርቱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ የላሉትን እጆቻችሁን የሰለሉትንም ጉልበቶቻችሁን አቅኑ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ የዛሉትን እጆቻችሁንና የደከሙትን ጒልበቶቻችሁን አበርቱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ የላሉትን እጆች የሰለሉትንም ጉልበቶች አቅኑ፤ |
እነርሱም፦ ስለ ምን ታለቅሳለህ? ቢሉህ አንተ እንዲህ በላቸው፦ ስለሚመጣው ወሬ ነው፤ ልብም ሁሉ ይቀልጣል፤ እጆችም ሁሉ ይዝላሉ፤ ሥጋና መንፈስ ሁሉ ይደክማል፤ ከጕልበትም እዥ ይፈስሳል፤ እነሆ ይመጣል፤ ይፈጸማልም፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ወንድሞች ሆይ! እንመክራችኋለን፤ ያለ ሥርዐት የሚሄዱትን ገሥጹአቸው፤ ድፍረት የሌላቸውን አጽኑአቸው፤ ለደካሞች ትጉላቸው፤ ሰውን ሁሉ ታገሡ።