እግዚአብሔርም ታላላቅ አንበሪዎችን፥ ውኃ ያስገኘውን ተንቀሳቃሽ ሕያው ፍጥረትን ሁሉ በየወገኑ፥ የሚበርሩ አዕዋፍንም ሁሉ በየወገናቸው ፈጠረ። እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ።
ዘፍጥረት 7:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አራዊትም ሁሉ በየወገናቸው፥ እንስሳትም ሁሉ በየወገናቸው፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱ ተንቀሳቃሾችም ሁሉ በየወገናቸው፥ ወፎችም ሁሉ በየወገናቸው፥ የሚበሩ ወፎችም ሁሉ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዱር እንስሳት ከየወገኑ፣ ከቤት እንስሳት ከየወገኑ፣ በምድር ላይ ከሚሳቡ ፍጥረታት ከየወገናቸው፣ ከወፎችም ከየወገናቸውና ክንፍ ያላቸው ሁሉ ዐብረዋቸው ገቡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእነርሱ ጋር፥ ከአራዊት፥ ከእንስሶች፥ በደረታቸው እየተሳቡ ከሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶችና በሰማይ ከሚበርሩ ወፎች ከእያንዳንዱ ዓይነት አብረዋቸው ገቡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከአራዊት፥ ከእንስሶች፥ በደረታቸው እየተሳቡ ከሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶችና በሰማይ ከሚበርሩ ወፎች ከእያንዳንዱ ዐይነት አብረዋቸው ገቡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱ አራዊትም ሂሉ በየወገናቸው፤ እንስሳትም ሁሉ በየወገናቸው በንድር ላይ የሚንቀሳቀሱ ተንቀሳቃሾችም ሁሉ በየወገናቸው ወፎችም ሁሉ በየወገናቸው |
እግዚአብሔርም ታላላቅ አንበሪዎችን፥ ውኃ ያስገኘውን ተንቀሳቃሽ ሕያው ፍጥረትን ሁሉ በየወገኑ፥ የሚበርሩ አዕዋፍንም ሁሉ በየወገናቸው ፈጠረ። እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ።
እግዚአብሔርም አለ፥ “ምድር ሕያዋን ፍጥረታትን እንደ ወገኑ፥ እንስሳትንና ተንቀሳቃሾችን፥ የምድር አራዊትንም እንደየወገኑ ታውጣ፥” እንዲሁም ሆነ።
ከእንስሳ ሁሉ፥ ከተንቀሳቃሽ አራዊትም ሁሉ፥ ሥጋ ካለው ሁሉ ከአንተ ጋር ትመግባቸው ዘንድ ከሁሉም ሁለት ሁለት ወደ መርከብ ታገባለህ፤ ተባትና እንስት ይሁን።
በዚያውም ቀን ኖኅ ወደ መርከብ ገባ፤ የኖኅ ልጆችም ሴም፥ ካም፥ ያፌትና የኖኅ ሚስት፥ ሦስቱም የልጆቹ ሚስቶች ከእርሱ ጋር ገቡ።