ዘፍጥረት 50:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮሴፍም አባቱን ሊቀብር ወጣ፤ የፈርዖን ሎሌዎችም ሁሉ፥ የቤቱ ሽማግሌዎችም ሁሉ፥ የግብፅ ምድር ሽማግሌዎችም ሁሉ ከእርሱ ጋር ወጡ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ዮሴፍ አባቱን ለመቅበር ወጣ፤ የፈርዖን ሹማምት በሙሉ፣ የቤተ መንግሥቱ ከፍተኛ ባለሥልጣኖች እንዲሁም የግብጽ ከፍተኛ ባለሥልጣኖች ሁሉ ተከተሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮሴፍም አባቱን ሊቀብር ወጣ፥ የፈርዖን አገልጋዮቹም ሁሉ ከእርሱ ጋር ወጡ፥ የቤቱ ሽማግሌዎችና የግብጽ ምድር ሽማግሌዎችም ሁሉ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ዮሴፍ አባቱን ለመቅበር ሄደ፤ የፈርዖን ባለሥልጣኖችና በቤተ መንግሥቱ የሚገኙ ታላላቅ ሰዎች፥ ሌሎችም የግብጽ መኳንንት ዮሴፍን ተከትለው ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮሴፍም አባቱን ሊቀብር ወጣ የፈርዖን ሎላልትም ሁሉ ከእርሱ ጋር ወጡ የቤቱ ሽማግሌዎችም የግብፅ ምድር ሽማግሌዎችም ሁሉ፤ |
የዮሴፍም ቤተ ሰቦች ሁሉ፥ ወንድሞቹም፥ የአባቱም ቤተ ሰቦች ወጡ፤ ልጆቻቸውንና በጎቻቸውን፥ ከብቶቻቸውንም ብቻ በጌሤም ተዉ።