ዘፍጥረት 50:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የልቅሶውም ወራት ከተፈጸመ በኋላ ዮሴፍ ለፈርዖን መኳንንት እንዲህ ብሎ ተናገረ፥ “እኔ በፊታችሁ ሞገስን አግኝቼ እንደ ሆንሁ ለፈርዖን እንዲህ ብላችሁ ስለ እኔ ንገሩት፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሐዘኑ ጊዜ እንዳበቃ ዮሴፍ የፈርዖንን ቤተ ሰዎች እንዲህ አላቸው፤ “በፊታችሁ ሞገስ አግኝቼ ከሆነ፣ ለፈርዖን እንዲህ ብላችሁ ንገሩልኝ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የልቅሶውም ወራት ባለፈ ጊዜ ዮሴፍ ለፈርዖን ቤተሰቦች እንዲህ ብሎ ተናገረ፦ “እኔ በፊታችሁ ሞገስን አግኝቼ እንደሆን ለፈርዖን እንዲህ ብላችሁ ንገሩት፦ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የለቅሶው ወራት በተፈጸመ ጊዜ ዮሴፍ የፈርዖንን ባለ ሥልጣኖች እንዲህ አላቸው፦ “መልካም ፈቃዳችሁ ቢሆን እባካችሁ ለፈርዖን፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የልቅሶውም ወራት ባለፈ ጊዜ ዮሴፍ ለፈርዓን ቤተ ሰቦች እንዲህ ብሎ ተናገረ፦ እኔ በፊታችሁ ሞገስን አግኝቼ እንደ ሆንሁ ለፈርዖን እንዲህ ብላችሁ ንገሩት፦ |
አባቴ ሳይሞት አምሎኛል፤ እንዲህ ሲል፦ ‘እነሆ እኔ እሞታለሁ፤ በቈፈርሁት መቃብር በከነዓን ምድር በዚያ ቅበረኝ።’ አሁንም ወጥቼ አባቴን ልቅበርና ልመለስ።”