ልያም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅንም ወለደች፥ ስሙንም ሮቤል ብላ ጠራችው፥ “እግዚአብሔር መዋረዴን አይቶአልና፥ እንግዲህስ ወዲህ ባሌ ይወድደኛል” ስትል።
ዘፍጥረት 46:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከአባታቸው ከያዕቆብ ጋር ወደ ግብፅ የገቡት የእስራኤል ልጆች ስም ይህ ነው፤ ያዕቆብና ልጆቹ፤ የያዕቆብ በኵር ሮቤል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ግብጽ የወረዱት የእስራኤል ልጆች፣ ያዕቆብና ዘሮቹ እነዚህ ናቸው፦ የያዕቆብ የበኵር ልጅ ሮቤል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ግብጽም የገቡት የእስራኤል ልጆች ስም ይህ ነው፥ ያዕቆብና ልጆቹ፥ የያዕቆብ በኩር ሮቤል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእስራኤል ጋር ወደ ግብጽ የወረዱት የእስራኤላውያን ስም ዝርዝር የሚከተለው ነው፦ የያዕቆብ የበኲር ልጅ ሮቤል፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ግብፅም የገቡት የእስራኤል ልጆች ስም ይህ ነው ያዕቆብና ልጆቹ የያዕቆብ በኵር ሮቤል። |
ልያም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅንም ወለደች፥ ስሙንም ሮቤል ብላ ጠራችው፥ “እግዚአብሔር መዋረዴን አይቶአልና፥ እንግዲህስ ወዲህ ባሌ ይወድደኛል” ስትል።
ወንዶች ልጆቹንና የወንዶች ልጆቹን ወንዶች ልጆች፥ ሴቶች ልጆቹንና የሴቶች ልጆቹን ሴቶች ልጆች፥ ዘሩንም ሁሉ ከእርሱ ጋር ወደ ግብፅ አስገባቸው።