ዘፍጥረት 42:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሀገሩም ጌታ ያ ሰው እንዲህ አለን፦ ‘ሰላማውያን ሰዎች ከሆናችሁ በዚህ ዐውቃለሁ፤ አንደኛውን ወንድማችሁን ከእኔ ጋር ተዉት፤ ለቤታችሁም የሸመታችሁትን እህል ይዛችሁ ሂዱ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከዚህ በኋላ የአገሩ ጌታ የሆነው ሰው እንዲህ አለን፤ ‘ታማኝ ሰዎች መሆናችሁን የማውቀው በዚህ ነው፤ ከእናንተ መካከል አንዱን ወንድማችሁን እዚህ እኔ ዘንድ ትታችሁ የተቀራችሁት ለተራቡት ቤተ ሰቦቻችሁ እህል ይዛችሁላቸው ሂዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ከዚህ በኋላ የአገሩ ጌታ የሆነው ሰው እንዲህ አለን፤ ‘ታማኝ ሰዎች መሆናችሁን የማውቀው በዚህ ነው፤ ከእናንተ መካከል አንዱን ወንድማችሁን እዚህ እኔ ዘንድ ትታችሁ የተቀራችሁት ለተራቡት ቤተሰቦቻችሁ እህል ይዛችሁላቸው ሂዱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰውየውም እንዲህ አለን፤ ‘ታማኞች ሰዎች መሆናችሁን የማውቀው ይህን አንድ ነገር ብታደርጉ ነው፤ ይኸውም ከእናንተ አንዱ ከእኔ ጋር ይቈይ፤ ሌሎቻችሁ ለተራቡት ቤተሰቦቻችሁ እህል ይዛችሁ ወደ አገራችሁ ተመለሱ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአገሩም ጌታ ያ ስው እንዲህ አለን፦ የታመናችሁ ስዎች ከሆናችሁ በዚህ አውቃለሁ አንደኛውን ወንድማችሁን ከእኔ ጋር ተውት ለቤታችሁም ራብ እህልን ወስዳችሁ ሂዱ፤ |
እኛ የአባታችን ልጆች ዐሥራ ሁለት ወንድማማቾች ነን፤ አንዱ ሞቶአል፤ ታናሹም በከነዓን ምድር ዛሬ ከአባታችን ጋር አለ።