ወንድማችሁን ያመጣ ዘንድ ከእናንተ አንዱን ላኩ፤ እናንተ ግን እውነትን የምትናገሩ ከሆነ ወይም ከአልሆነ ነገራችሁ እስኪታወቅ ድረስ ከዚህ ተቀመጡ፤ ይህ ከአልሆነ ‘የፈርዖንን ሕይወት!’ ሰላዮች ናችሁ።”
ዘፍጥረት 42:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የሀገሩ ጌታ የሆነው ሰው በክፉ ንግግር ተናገረን፤ የምድሪቱም ሰላዮች እንደሆን አድርጎ ወደ እስር ቤት አስገባን።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የአገሩ ጌታ የሆነው ሰው ምድሪቱን እንደምንሰልል ቈጥሮን በቍጣ ተናገረን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የአገሩ ጌታ የሆነው ሰው ምድሪቱን እንደምንሰልል ቈጥሮን በቁጣ ተናገረን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የግብጽ አገር አስተዳዳሪ ‘አገሬን ልትሰልሉ የመጣችሁ ናችሁ’ በማለት በቊጣ ቃል ተናገረን፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአገሩ ጌታ የሆነው ሰው በክፋ ንግግር ተናገረን የምድሪቱም ሰላዮች አስመሰለን። |
ወንድማችሁን ያመጣ ዘንድ ከእናንተ አንዱን ላኩ፤ እናንተ ግን እውነትን የምትናገሩ ከሆነ ወይም ከአልሆነ ነገራችሁ እስኪታወቅ ድረስ ከዚህ ተቀመጡ፤ ይህ ከአልሆነ ‘የፈርዖንን ሕይወት!’ ሰላዮች ናችሁ።”
ዮሴፍም ወንድሞቹን በአያቸው ጊዜ ዐወቃቸው፤ እንደማያውቃቸውም ሆነ፤ ክፉ ቃልንም ተናገራቸው፥ “እናንተ ከወዴት መጣችሁ?” አላቸው። እነርሱም፥ “ከከነዓን ምድር እህል ልንሸምት የመጣን ነን” አሉት።