ዘፍጥረት 41:47 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሰባቱም የጥጋብ ዓመታት ግብፅ ያስገኘችው እህል ሁሉ ክምር ሆነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሰባቱም የጥጋብ ዓመታት ምድሪቱ የተትረፈረፈ ሰብል ሰጠች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሰባቱም የጥጋብ ዓመታት ምድሪቱ የተትረፈረፈ ሰብል ሰጠች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሰባቱ የጥጋብ ዓመቶች ምድሪቱ እጅግ ብዙ ሰብል ሰጠች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮሴፍም ከፈርዖን ፊት ወጣ የግብፅ ምድርንም ሁሉ ዞረ። በሰባቱም በጥጋብ ዓመታት የምድሪቱ ፍሬ ክምር ሆነ። |
ዮሴፍም በግብፅ ንጉሥ በፈርዖን ፊት በቆመ ጊዜ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበረ። ዮሴፍም ከፈርዖን ፊት ወጣ፤ የግብፅ ምድርንም ሁሉ ዞረ።
በግብፅ ምድር ሁሉ ያለውን የሰባቱን የጥጋብ ዓመታት እህል ሁሉ ሰበሰበ፤ እህልንም በከተሞቹ አደለበ፤ በየከተማይቱም ዙሪያ ያለውን የእርሻውን እህል ሁሉ በዚያው ከተተ።