ብላቴናውም ይህን ነገር ያደርግ ዘንድ አልዘገየም፤ የያዕቆብን ልጅ ወድዶአልና፤ እርሱም ከአባቱ ቤተ ሰብእ ሁሉ የከበረ ነበረ።
ዘፍጥረት 41:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነዚያ የከሱትና መልከ ክፉዎቹ ላሞች እነዚያን የመጀመሪያዎቹን ያማሩና የወፈሩ ሰባት ላሞች ዋጡአቸው፤ በሆዳቸውም ተዋጡ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐጥንታቸው የወጣና አስከፊ መልክ ያላቸው ላሞች መጀመሪያ የወጡትን፣ ሥጋቸው የወፈረውን ሰባቱን ላሞች ዋጧቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዐጥንታቸው የወጣና አስከፊ መልክ ያላቸው ላሞች መጀመሪያ የወጡትን፥ ሥጋቸው የወፈረውን ሰባቱን ላሞች ዋጧቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የከሱትና አስከፊ የሆኑት ላሞች በመጀመሪያ የወጡትን ሰባት የወፈሩ ላሞች ዋጡአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የከሱትና መልከ ክፋዎቹ ላሞች የመጀመሪያዎቹን ወፍራሞቹን ስባት ላሞች ዋጡአቸው፥ |
ብላቴናውም ይህን ነገር ያደርግ ዘንድ አልዘገየም፤ የያዕቆብን ልጅ ወድዶአልና፤ እርሱም ከአባቱ ቤተ ሰብእ ሁሉ የከበረ ነበረ።
ከእነርሱም በኋላ እነሆ፥ የደከሙ፥ መልካቸውም እጅግ የከፋ፥ ሥጋቸውም የከሳ ሌሎች ሰባት ላሞች ከወንዙ ወጡ፤ በግብፅም ምድር ሁሉ እንደ እነርሱ መልከ ክፉ ከቶ አላየሁም፤
በሆዳቸውም ውስጥ የገባ እንደሌለ ሆኑ፤ መልካቸውም በመጀመሪያ እንደ ነበረው የከፋ ነበረ፤ ነቃሁም። ዳግመኛም ተኛሁ፤
ከእነርሱም በኋላ እነሆ፥ መልካቸው የከፋ፥ ሥጋቸውም የከሳ ሌሎች ሰባት ላሞች ከወንዙ ወጡ፤ በእነዚያም ላሞች አጠገብ በወንዙ ዳር ተሰማርተው ነበር።