La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 41:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በዚ​ያም የእ​ን​ጀራ አበ​ዛ​ዎች አለቃ አገ​ል​ጋይ የሆነ አንድ ዕብ​ራዊ ጐል​ማሳ ከእኛ ጋር ነበር፤ ለእ​ር​ሱም ነገ​ር​ነው፤ ሕል​ማ​ች​ን​ንም ተረ​ጐ​መ​ልን።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በዚያ ጊዜ የዘበኞች አለቃ አገልጋይ የሆነ አንድ ዕብራዊ ወጣት ከእኛ ጋራ እስር ቤት ነበር። ሕልማችንን በነገርነው ጊዜ፣ ፍችውን ነገረን፤ ለእያንዳንዳችንም እንደ ሕልማችን ተረጐመልን፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በዚያን ጊዜ የዘበኞች አለቃ አገልጋይ የሆነ አንድ ዕብራዊ ወጣት ከእኛ ጋር እስር ቤት ነበር። ሕልማችንን በነገርነው ጊዜ፥ ፍቺውን ነገረን፤ ለእያንዳንዳችንም እንደ ሕልማችን ተረጐመልን፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የዘበኞች አለቃ አገልጋይ የነበረ አንድ ወጣት ዕብራዊ ከእኛ ጋር በእስር ቤት ነበር፤ የእያንዳንዳችንን ሕልም ለእርሱ ነገርነውና ተረጐመልን።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በዚይም የዘበኞቹ አለቃ ባሪያ የሆነ አንድ ዕብራዊ ጕልማሳ ከእኛ ጋር ነበረ ለእርሱም ነገር ነው ሕልማችንንም፥ ተረጎመልን።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 41:12
5 Referencias Cruzadas  

እነ​ዚያ ይስ​ማ​ኤ​ላ​ው​ያን ሰዎች ግን ዮሴ​ፍን በግ​ብፅ ለፈ​ር​ዖን ጃን​ደ​ረባ ለዘ​በ​ኞቹ አለቃ ለጲ​ጥ​ፋራ ሸጡት።


ዮሴፍ ግን ወደ ግብፅ ወረደ፤ የፈ​ር​ዖን ጃን​ደ​ረባ የመ​ጋ​ቢ​ዎ​ቹም አለቃ የሚ​ሆን የግ​ብፅ ሰው ጲጥ​ፋራ ወደ ግብፅ ከአ​ወ​ረ​ዱት ከይ​ስ​ማ​ኤ​ላ​ው​ያን እጅ ገዛው።


ዮሴ​ፍ​ንም ወሰ​ደው፤ የን​ጉሡ እስ​ረ​ኞች ወደ​ሚ​ታ​ሰ​ሩ​በት ስፍራ ወደ ግዞት ቤትም አገ​ባው፤ ከዚ​ያም በግ​ዞት ነበረ።