ፈርዖን በአገልጋዮቹ ላይ ተቈጣ፤ እኔንም የእንጀራ አበዛዎቹንም አለቃ በግዞት ቤት አኖረን፤
በአንድ ወቅት ፈርዖን እኔንና የእንጀራ ቤት አዛዡን ተቈጥቶ በዘበኞቹ አለቃ ግቢ አስሮን ነበር።
ንጉሥ ሆይ፥ አንተ በእኔና በእንጀራ ቤት ኀላፊው ላይ ተቈጥተህ በዘበኞች አለቃ ቤት እንድንታሰር አድርገህ ነበር፤
ፈርዖን በባሪይዎቹ ላይ ተቆጣ እኔንም የእንጀራ አበዛዎቹንም አለቃ በግዞት ስፍራ በዘበኞች አለቃ ቤት አኖረን
እነዚያ ይስማኤላውያን ሰዎች ግን ዮሴፍን በግብፅ ለፈርዖን ጃንደረባ ለዘበኞቹ አለቃ ለጲጥፋራ ሸጡት።
ዮሴፍንም ወሰደው፤ የንጉሡ እስረኞች ወደሚታሰሩበት ስፍራ ወደ ግዞት ቤትም አገባው፤ ከዚያም በግዞት ነበረ።