La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 38:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እር​ስ​ዋም ሲወ​ስ​ዱ​አት ወደ አማቷ እን​ዲህ ብላ ላከች፤ “ተመ​ል​ከት፦ ይህ ቀለ​በት፥ ይህ ኩፌት፥ ይህ በትር የማን ነው? ይህስ ፅንስ የማን ነው?”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እርሷም ተይዛ በምትወሰድበት ጊዜ ለዐማቷ፣ “እኔ ያረገዝሁት የእነዚህ ዕቃዎች ባለቤት ከሆነ ሰው ነው” ስትል ላከችበት፤ ደግሞም፣ “የማኅተሙ ቀለበት ከነማንጠልጠያውና በትሩ የማን እንደ ሆነ እስኪ ተመልከት” አለችው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እርሷም ተይዛ በምትወሰድበት ጊዜ ለዐማትዋ፥ “እኔ ያረገዝሁት የእነዚህ ዕቃዎች ባለቤት ከሆነ ሰው ነው” ስትል ላከችበት፤ ደግሞም፥ “የማኅተሙ ቀለበት ከነማንጠልጠያውና በትሩ የማን እንደሆነ እስቲ ተመልከት” አለችው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እርስዋም ተይዛ ውጪ በምትወጣበት ጊዜ “እኔ የፀነስኩት የእነዚህ ዕቃዎች ባለቤት ከሆነ ሰው ነው፤ ይህን የማኅተም ቀለበት ከነማሰሪያውና ይህንንም በትር ተመልክተህ የማን እንደ ሆኑ ዕወቅ” ብላ ለዐማቷ ለይሁዳ ላከችለት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እርስዋም ባወጡአት ጊዜ ወደ አማትዋ እንዲህ ብላ ላከች፦ ለዚህ ለባለ ገንዘብ ነው የፀነስሁት፤ ተመልከት፤ ይህ ቀለበት ይህ አምባር፤ ይህ በትር የማን ነው?

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 38:25
7 Referencias Cruzadas  

ብዙ ኅብር ያለ​በ​ትን ቀሚ​ሱ​ንም ላኩ፤ ወደ አባ​ታ​ቸ​ውም አገ​ቡት፤ እን​ዲ​ህም አሉት፥ “ይህን ልብስ አገ​ኘን፤ ይህ የል​ጅህ ልብስ እንደ ሆነ ወይም እን​ዳ​ል​ሆነ እስኪ እየው?”


እር​ሱም፥ “ምን መያዣ ልስ​ጥሽ?” አላት። እር​ስ​ዋም፥ “ቀለ​በ​ት​ህን፥ ኩፌ​ት​ህን፥ በእ​ጅህ ያለ​ውን በትር” አለች። እር​ሱም ሰጣ​ትና ከእ​ር​ስዋ ደረሰ፤ እር​ስ​ዋም ፀነ​ሰ​ች​ለት።


ሌባ በተ​ያዘ ጊዜ እን​ደ​ሚ​ያ​ፍር፤ እን​ዲሁ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች፥ እነ​ር​ሱና ንጉ​ሦ​ቻ​ቸ​ውም፥ አለ​ቆ​ቻ​ቸ​ውም፥ ካህ​ና​ቶ​ቻ​ቸ​ውም፥ ነቢ​ያ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ያፍ​ራሉ።


ይህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ እኔ በወ​ን​ጌል እን​ዳ​ስ​ተ​ማ​ርሁ ሰዎ​ችን በል​ቡ​ና​ቸው የሰ​ወ​ሩ​ት​ንና የሸ​ሸ​ጉ​ትን በሚ​መ​ረ​ም​ር​በት ጊዜ የሚ​ና​ገ​ሩ​ትና የሚ​መ​ል​ሱት እን​ደ​ሌለ ስለ​ሚ​ያ​ውቁ ነው።


ጊዜው ሳይ​ደ​ርስ ዛሬ ለምን ትመ​ረ​ም​ራ​ላ​ቸሁ? በጨ​ለማ ውስጥ የተ​ሰ​ወ​ረ​ው​ንም የሚ​ያ​በራ፥ የል​ብን አሳ​ብም የሚ​ገ​ልጥ ጌታ​ችን ይመ​ጣል፤ ያን​ጊዜ ሁሉም ዋጋ​ውን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ይቀ​በ​ላል።


ሙታንንም ታናናሾችንና ታላላቆችን በዙፋኑ ፊት ቆመው አየሁ፤ መጻሕፍትም ተከፈቱ፤ ሌላ መጽሐፍም ተከፈተ፤ እርሱም የሕይወት መጽሐፍ ነው፤ ሙታንም በመጻሕፍት ተጽፎ እንደ ነበረ እንደ ሥራቸው መጠን ተከፈሉ።