እርስዋም የመበለትነቷን ልብስ አወለቀች፤ መጐናጸፊያዋንም ለበሰች፤ ተሸፈነችም፤ ወደ ተምናም በሚወስደው መንገድ ዳር በኤናይም ደጅ ተቀመጠች፤ ሴሎም እንደ አደገ፥ ሚስትም ትሆነው ዘንድ እርስዋን ሊሰጠው እንዳልፈለገ አይታለችና።
ዘፍጥረት 38:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስዋም ተነሥታ ሄደች፤ መጐናጸፊያዋንም አውልቃ የመበለትነቷን ልብስ ለበሰች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ወደ መኖሪያዋ ተመልሳ፣ ሻሿን አውልቃ እንደ ወትሮዋ የመበለት ልብሷን ለበሰች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ወደ መኖሪያዋ ተመልሳ፥ ሻሽዋን አውልቃ እንደ ወትሮዋ የመበለት ልብሷን ለበሰች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያ በኋላ ሻሽዋን ከፊቷ ላይ አንሥታ የመበለትነት ልብሷን እንደገና ለበሰች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤስውም ተነሥታ ሄደች መጎናጸፊያዋንም አውልቃ የመበለትነትዋን ልብስ ለበስች። |
እርስዋም የመበለትነቷን ልብስ አወለቀች፤ መጐናጸፊያዋንም ለበሰች፤ ተሸፈነችም፤ ወደ ተምናም በሚወስደው መንገድ ዳር በኤናይም ደጅ ተቀመጠች፤ ሴሎም እንደ አደገ፥ ሚስትም ትሆነው ዘንድ እርስዋን ሊሰጠው እንዳልፈለገ አይታለችና።
እርሱም፥ “ምን መያዣ ልስጥሽ?” አላት። እርስዋም፥ “ቀለበትህን፥ ኩፌትህን፥ በእጅህ ያለውን በትር” አለች። እርሱም ሰጣትና ከእርስዋ ደረሰ፤ እርስዋም ፀነሰችለት።
ይሁዳም መያዣውን ከሴቲቱ እጅ ይቀበል ዘንድ በበግ ጠባቂው በዓዶሎማዊው እጅ የፍየሉን ጠቦት ላከላት፤ እርስዋንም አላገኛትም።
ኢዮአብም ወደ ቴቁሔ ልኮ ከዚያ ብልሃተኛ ሴት አስመጣና፥ “አልቅሺ፤ የኀዘንም ልብስ ልበሺ፤ ዘይትም አትቀቢ፤ ስለ ሞተ ሰውም ብዙ ዘመን እንደምታለቅስ ሴት ሁኚ፤