ወደ እርስዋም አዘነበለ፥ “እባክሽ ወደ አንቺ ልግባ አላት፤” እርስዋ ምራቱ እንደ ሆነች አላወቀም ነበርና። እርስዋም፥ “ወደ እኔ ብትገባ ምን ትሰጠኛለህ?” አለችው።
ዘፍጥረት 38:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የፍየል ጠቦት ከመንጋዬ እልክልሻለሁ” አላት። እርስዋም፥ “እስክትልክልኝ ድረስ መያዣ ስጠኝ” አለችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከመንጋዬ መካከል አንድ የፍየል ጠቦት እልክልሻለሁ” አላት። እርሷም መልሳ፣ “ጠቦቱን እስክትልክልኝ ድረስ ምን መያዣ ትሰጠኛለህ?” ብላ ጠየቀችው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ከመንጋዬ መካከል አንድ የፍየል ጠቦት እልክልሻለሁ” አላት። እርሷም መልሳ፥ “ጠቦቱን እስክትልክልኝ ድረስ ምን መያዣ ትሰጠኛለህ?” ብላ ጠየቀችው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም “ከመንጋዎቼ መካከል አንድ የፍየል ጠቦት እልክልሻለሁ” አላት። እርስዋም “እሺ እንግዲያውስ ጠቦቱን እስክትልክልኝ ድረስ መያዣ የሚሆን ነገር ስጠኝ” አለችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የፍየል ጠቦት ከመንጋዬ እሰድድልሻለሁ አላት። እርስዋም፦ እስክትሰደድልኝ ድረስ መያዣ ትሰጠኛለህን? አለችው። |
ወደ እርስዋም አዘነበለ፥ “እባክሽ ወደ አንቺ ልግባ አላት፤” እርስዋ ምራቱ እንደ ሆነች አላወቀም ነበርና። እርስዋም፥ “ወደ እኔ ብትገባ ምን ትሰጠኛለህ?” አለችው።
እርሱም፥ “ምን መያዣ ልስጥሽ?” አላት። እርስዋም፥ “ቀለበትህን፥ ኩፌትህን፥ በእጅህ ያለውን በትር” አለች። እርሱም ሰጣትና ከእርስዋ ደረሰ፤ እርስዋም ፀነሰችለት።
ይሁዳም መያዣውን ከሴቲቱ እጅ ይቀበል ዘንድ በበግ ጠባቂው በዓዶሎማዊው እጅ የፍየሉን ጠቦት ላከላት፤ እርስዋንም አላገኛትም።
ለአመንዝራዎች ሁሉ ዋጋ ይሰጡአቸዋል፤ አንቺ ግን ለወዳጆችሽ ሁሉ ዋጋ ትሰጫለሽ፤ ከአንቺም ጋር ለማመንዘር በዙሪያሽ ይገቡብሽ ዘንድ መማለጃን ትሰጫቸዋለሽ።
ጌታውም ዐመፀኛውን መጋቢ እንደ ብልህ ሰው ስለ ሠራ አመሰገነው፤ ከብርሃን ልጆች ይልቅ የዚህ ዓለም ልጆች በዓለማቸው ይራቀቃሉና።
ከጊዜም በኋላ በስንዴ መከር ጊዜ ሶምሶን የፍየል ጠቦት ይዞ ሚስቱን ሊጠይቅ ሄደና፥ “ወደ ጫጕላ ቤት ወደ ሚስቴ ልግባ” አለ፤ አባቷ ግን እንዳይገባ ከለከለው።