ኑ፥ እንግደለውና በአንድ ጕድጓድ ውስጥ እንጣለው፤ ክፉ አውሬም በላው እንላለን፤ ሕልሞቹም ምን እንደሚሆኑ እናያለን።”
ዘፍጥረት 37:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብዙ ኅብር ያለበትን ቀሚሱንም ላኩ፤ ወደ አባታቸውም አገቡት፤ እንዲህም አሉት፥ “ይህን ልብስ አገኘን፤ ይህ የልጅህ ልብስ እንደ ሆነ ወይም እንዳልሆነ እስኪ እየው?” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በኅብረ ቀለማት ያጌጠችውን እጀ ጠባብ ወደ አባታቸው ወስደው፣ “ይህን ወድቆ አገኘነው፤ የልጅህ እጀ ጠባብ መሆን አለመሆኑን እስኪ እየው” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብዙ ኅብር ያለበትንም ልብሱን ወደ አባታቸው ወስደው “እነሆ፥ ይህን አገኘን የልጅህ ልብስ እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ እይ” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብዙ ኅብር ያለበትንም ልብሱን ወደ አባታቸው ወስደው “እነሆ፥ ይህን አገኘን የልጅህ ልብስ እንደ ሆነ ወይም እንዳልሆነ እይ” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብዙ ኅብር ያለበት ቀሚሱንም ላኩ፥ ወደ አባታቸውም አገቡት እንዲህም አሉት፦ ይህንን አገኘነ ይህ የልጅህ ልብስ እንደ ሆነ ወይም እንዳልሆነ እስኪ እየው። |
ኑ፥ እንግደለውና በአንድ ጕድጓድ ውስጥ እንጣለው፤ ክፉ አውሬም በላው እንላለን፤ ሕልሞቹም ምን እንደሚሆኑ እናያለን።”
ያዕቆብም ዮሴፍን ከልጆቹ ሁሉ ይልቅ ይወድደው ነበር፤ እርሱ በሽምግልናው የወለደው ነበርና። በብዙ ኅብር ያጌጠችም ቀሚስ አደረገለት።
እርስዋም ሲወስዱአት ወደ አማቷ እንዲህ ብላ ላከች፤ “ተመልከት፦ ይህ ቀለበት፥ ይህ ኩፌት፥ ይህ በትር የማን ነው? ይህስ ፅንስ የማን ነው?”