ያዕቆብም አለው፥ “እንዴት እንዳገለገልሁህ፥ በእኔ ዘንድ ያሉ ከብቶችህ ምን ያህል እንደ ሆኑ አታውቅምን? ጥቂት ሆነው አግኝቻቸዋለሁና፤
ዘፍጥረት 30:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁን ግን ፈጽመው በዝተዋል፤ እግዚአብሔርም በእኔ መምጣት ባርኮአቸዋል፤ አሁን ደግሞ ለቤቴ የምሠራው መቼ ነው?” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔ ከመምጣቴ በፊት ጥቂት የነበረው ሀብትህ ዛሬ ተትረፍርፏል፣ በተሰማራሁበት ሁሉ እግዚአብሔር በረከቱን አብዝቶልሃል። ታዲያ፣ ስለ ራሴ ቤት የማስበው መቼ ነው?” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእኔ መምጣት በፊት የነበረህ ጥቂት ነበርና፥ ዛሬም እጅግ በዛ፥ ወደ አንተ በመምጣቴም እግዚአብሔር ባረክህ፥ አሁንም እኔ ደግሞ ለቤቴ የምሠራው መቼ ነው?” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ ከመምጣቴ በፊት ጥቂት የነበሩት መንጋዎችህ አሁን እጅግ በዝተዋል፤ እኔ በደረስኩበት ስፍራ ሁሉ እግዚአብሔር በረከትን ሰጥቶሃል፤ የምሠራውስ መቼ ለቤተሰቤ የሚጠቅም ነገር ነው?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእኔ መምጣት በፊት የነበረህ ጥቂት ነበርና፥ ዛሬም እጅግ በዛ፤ ወደ አንተ በመምጣቴ እግዚአብሔር ባረክህ፤ አሁንም እኔ ደግሞ ለቤቴ የምሠራው መቼ ነው? |
ያዕቆብም አለው፥ “እንዴት እንዳገለገልሁህ፥ በእኔ ዘንድ ያሉ ከብቶችህ ምን ያህል እንደ ሆኑ አታውቅምን? ጥቂት ሆነው አግኝቻቸዋለሁና፤
ላባም፥ “የምሰጥህ ምንድን ነው?” አለው። ያዕቆብም አለው፥ “ምንም አትስጠኝ፤ ይህንም ነገር ብታደርግልኝ እንደገና በጎችህን አሰማራለሁ፤ እጠብቃለሁም።
ያዕቆብም እጅግ ባለጠጋ ሆነ፤ ሴቶችም ወንዶችም አገልጋዮች፥ ብዙ ከብትም፤ ላሞችም፥ በጎችም፥ ግመሎችና አህዮችም ሆኑለት።
እነሆ ወደ እናንተ ልመጣ ስዘጋጅ ይህ ሦስተኛዬ ነው፤ ነገር ግን አልተፋጠንሁም ገንዘባችሁን ያይደለ፥ እናንተን እሻለሁና፤ ልጆች ለወላጆቻቸው ያይደለ ወላጆች ለልጆቻቸው ሊያከማቹ ይገባልና፤
ትወርሳት ዘንድ የምትገባባት ምድር፥ በአትክልት ስፍራ እንደሚዘሩ ዘርህን እንደ ዘራህባት፥ በእግርህም እንዳጠጣሃት፥ እንደ ወጣህባት እንደ ግብፅ ምድር አይደለችም።