ዘፍጥረት 21:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የባሪያዪቱን ልጅ ደግሞ ታላቅ ሕዝብ አደርገዋለሁ፤ ዘርህ ነውና።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአገልጋይህም ልጅ የራስህ ልጅ ስለ ሆነ፣ እርሱንም ታላቅ ሕዝብ አደርገዋለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የባርያይቱን ልጅ ደግሞ ሕዝብ አደርገዋለሁ፥ ዘርህ ነውና።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአገልጋይቱም ልጅ የአንተ ልጅ ስለ ሆነ ታላቅ ሕዝብ እስኪሆን ድረስ ዘሩን አበዛለሁ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የባሪያይቱን ልጅ ደግሞ ሕዝብ አደርገዋለሁ ዘርህ ነውና። |
ስለ ይስማኤልም እነሆ፥ ሰምቼሃለሁ፤ እባርከዋለሁ፤ አበዛዋለሁ፤ እጅግም አበዛዋለሁ፤ ዐሥራ ሁለት አለቆችንም ይወልዳል፤ ታላቅ ሕዝብም አደርገዋለሁ።
አብርሃምም ማልዶ ተነሣ፤ እንጀራንም ወሰደ፤ የውኃ አቍማዳንም ለአጋር በትከሻዋ አሸከማት፤ ሕፃኑንም ሰጥቶ አስወጣት፤ እርስዋም ሄደች፤ በዐዘቅተ መሐላም በኩል ባለው ምድረ በዳ ተቅበዘበዘች።