እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው፥ “እሺ እነሆ፥ ሚስትህ ሣራ ወንድ ልጅን ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ይስሐቅ ብለህ ትጠራዋለህ፤ ለእርሱና ከእርሱ በኋላ ለዘሩ አምላክ እሆን ዘንድ ቃል ኪዳኔን ለዘለዓለም ቃል ኪዳን ከእርሱ ጋር አቆማለሁ።
ዘፍጥረት 21:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው፥ “ስለዚች አገልጋይህና ስለ ሕፃኑ አትዘን፤ ሣራም የምትነግርህን ቃል ሁሉ ስማ፤ በይስሐቅ ዘር ይጠራልሃልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም አብርሃምን እንዲህ አለው፤ “ስለ ልጁም ሆነ ስለ አገልጋይህ ሐሳብ አይግባህ፤ ዘር የሚጠራልህ በይሥሐቅ በኩል ስለ ሆነ፣ ሣራ የምትልህን ሁሉ ስማ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው “ስለ ባርያህና ስለ ብላቴናው አትዘን፥ ሣራም የምትነግርህን ቃል ሁሉ ስማ፥ በይስሐቅ ዘር ይጠራልሃልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ግን አብርሃምን “ስለ ልጁና ስለ አገልጋይቱ ስለ አጋር አትጨነቅ፤ ዘር የሚወጣልህ በይስሐቅ በኩል ስለ ሆነ ሣራ የምትልህን ሁሉ አድርግ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው ስለ ባሪያህና ስለ ብላቴናው አትዘን፤ ሣራም የምትነግርህን ቃል ሁሉ ስማ በይስሐቅ ዘር ይጠራልሃልና። |
እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው፥ “እሺ እነሆ፥ ሚስትህ ሣራ ወንድ ልጅን ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ይስሐቅ ብለህ ትጠራዋለህ፤ ለእርሱና ከእርሱ በኋላ ለዘሩ አምላክ እሆን ዘንድ ቃል ኪዳኔን ለዘለዓለም ቃል ኪዳን ከእርሱ ጋር አቆማለሁ።
በመጀመሪያ መጨረሻውን፥ ከጥንትም ያልተደረገውን እናገራለሁ፤ ምክሬ ትጸናለች፤ የመከርሁትንም ሁሉ አደርጋለሁ እላለሁ።
ነገር ግን መጽሐፍ ምን ይላል? “የባሪያዪቱ ልጅ ከእመቤቲቱ ልጅ ጋር አይወርስምና ባሪያዪቱን ከልጅዋ ጋር አስወጥተህ ስደዳት”
እግዚአብሔርም ሳሙኤልን አለው፥ “በእነርሱ ላይ እንዳልነግሥ እኔን ናቁ እንጂ አንተን አልናቁምና በሚሉህ ነገር ሁሉ የሕዝቡን ቃል ስማ።
አሁንም ቃላቸውን ስማ፤ ነገር ግን ጽኑ ምስክር መስክርባቸው፤ በእነርሱም ላይ የሚነግሠውን የንጉሡን ሥርዐት ንገራቸው።”