ከእነዚያ አምሳ ጻድቃን አምስት ቢጐድሉ ከተማዪቱን ሁሉ በጐደሉት በአምስቱ ምክንያት ታጠፋለህን?” እግዚአብሔርም፥ “ከዚያ አርባ አምስት ባገኝ ስለ እነርሱ አላጠፋትም” አለው።
ዘፍጥረት 18:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብርሃምም አለው፥ “ከዚያ አርባ ቢገኙሳ?” እግዚአብሔርም፥ “ለአርባው ስል አላጠፋትም” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አብርሃምም እንደ ገና፣ “ምናልባት አርባ ጻድቃን ቢገኙስ?” አለ። እርሱም፣ “ለአርባው ስል እምራታለሁ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደግሞም ተናገረው፥ እንዲህም አለ፦ “ምናልባት ከዚያ አርባ ቢገኙሳ?” እርሱም፦ “ለአርባው ስል አላደርገውም” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አብርሃምም “አርባ ብቻ እዚያ ቢገኙስ?” ብሎ እንደገና ጠየቀ። እግዚአብሔርም “አርባ ቢገኙ ለእነርሱ ስል ከተማይቱን አላጠፋም” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞም ተናገረው እንዲህም አለ፤ ምናልባት ከዚይ አርባ ቢገኙሳ? እርሱም ለአርባው ስል አላደርገውም አለ። |
ከእነዚያ አምሳ ጻድቃን አምስት ቢጐድሉ ከተማዪቱን ሁሉ በጐደሉት በአምስቱ ምክንያት ታጠፋለህን?” እግዚአብሔርም፥ “ከዚያ አርባ አምስት ባገኝ ስለ እነርሱ አላጠፋትም” አለው።
አብርሃምም እንደገና ነገሩን ደገመ፤ እንዲህም አለው፥ “ከዚያ ሠላሳ ቢገኙሳ?” እርሱም፥ “ስለ ሠላሳው አላጠፋትም” አለው።
እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል፥ በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ፥ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ።