ዘፍጥረት 10:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጋሜርም ልጆች አስከናዝ፥ ሪፋት፥ ቴርጋማ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጎሜር ልጆች፦ አስከናዝ፣ ሪፋት፣ ቶጋርማ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጎሜር ልጆች፦ አሽከናዝ፥ ሪፋት እና ቶጋርማ ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጎሜር ልጆች፦ አሽከናዝ፥ ሪፋትና ቶጋርማ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጋሜርም ልጆች አስከናዝ፥ ሪፋት፥ ቴርጋማ ናቸው። |
“በምድር ላይ ዓላማን አንሡ፤ በአሕዛብም መካከል መለከትን ንፉ፤ አሕዛብንም ለዩባት፤ የአራራትንና የሚኒን የአስከናዝንም መንግሥታት እዘዙባት፤ ጦረኞችንም በላይዋ አቁሙ፤ ብዛታቸው እንደ አንበጣ የሆኑ ፈረሶችን በላይዋ አውጡ።
ጎሜርንና ከእርሱ ጋር ያሉትን ሁሉ፥ በሰሜን ዳርቻም ያለውን የቴርጋማን ቤትና ጭፍሮቹን ሁሉ፥ ብዙዎችንም ሕዝቦች ከአንተ ጋር አወጣለሁ።