የኖኅ ልጆች የሴም፥ የካምና፥ የያፌት ትውልድ ይህ ነው፤ ከጥፋት ውኃም በኋላ ልጆች ተወለዱላቸው።
የኖኅ ልጆች የሴም፣ የካምና የያፌት ትውልድ ይህ ነው፤ እነርሱም ራሳቸው ከጥፋት ውሃ በኋላ ወንዶች ልጆችን ወለዱ።
የኖኅ ልጆች የሴም፥ የካም፥ እና የያፌት ትውልድ ይህ ነው፥ ከጥፋት ውኃም በኋላ ልጆችን ወለዱ።
የኖኅ ልጆች የሴም፥ የካምና የያፌት ዘሮች የሚከተሉት ናቸው፤ እነዚህ ሦስቱ ከጥፋት ውሃ በኋላ ልጆችን ወለዱ፤
የኖኅ ልጆች የሴም የካም የያፌት ትውልድ ይህ ነው፤ ከጥፋት ውኃም በኍላ ልጆች ተወለዱላቸው።
የያፌት ልጆች ጋሜር፥ ማጎግ፥ ማዴ፥ ይህያን፥ ይልሳ፥ ቶቤል፥ሞሳሕ፥ ቴራስ ናቸው።
እግዚአብሔር አምላክ ሰማይንና ምድርን በፈጠረበት ቀን፥ በተፈጠሩ ጊዜ የሰማይና የምድር ፍጥረት ይህ ነው።
የሰዎች የትውልድ መጽሐፍ ይህ ነው። እግዚአብሔር አዳምን በፈጠረ ቀን በእግዚአብሔር ምሳሌ አደረገው፤
ለኖኅም አምስት መቶ ዓመት ሆነው፤ ኖህም ሦስት ልጆችን ወለደ፤ እነርሱም ሴም፥ ካምና ያፌት ናቸው።
የኖኅ ትውልድ እንዲህ ነው። ኖኅም በትውልዱ ጻድቅ፥ ፍጹምም ሰው ነበረ፤ ኖኅም እግዚአብሔርን ደስ አሰኘው።
እግዚአብሔርም ኖኅንና ልጆቹን ባረካቸው፤ እንዲህም አላቸው፥ “ብዙ፤ ተባዙ፤ ምድርንም ሙሉአት፤ ግዙአትም።
በምድር ሁሉ ላይ የተበተኑ የኖኅ ልጆች እነዚህ ሦስቱ ናቸው።
ኖኅም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ አምሳ ዓመት ሆነ፤ ሞተም።
እናንተም ብዙ፤ ተባዙ፤ ምድርንም ሙሉአት፤ ግዙአትም።”
አዳም፥ ሴት፥ ሄኖስ፥
ኖኅ፥ ልጆቹም ሴም፥ ካም፥ ያፌት።
የዳዊት ልጅ የአብርሃም ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ትውልድ መጽሐፍ።