La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፀአት 5:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አሠ​ሪ​ዎ​ቹም፥ “ገለባ ትቀ​በ​ሉ​በት እን​ደ​ነ​በረ ጊዜ የቀን ሥራ​ች​ሁን ጨርሱ” እያሉ ያስ​ቸ​ኩ​ሉ​አ​ቸው ነበር።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የባሪያ ተቈጣጣሪዎቹም “በየዕለቱ መሥራት የሚገባችሁ ሥራ ቀድሞ ጭድ ስናቀርብላችሁ ከምትሠሩት ሥራ ማነስ የለበትም” እያሉ ያጣድፏቸው ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አስገባሪዎቹም፦ “ገለባ ትቀበሉበት እንደ ነበረ ጊዜ የቀን ሥራችሁን ጨርሱ” እያሉ አስቸኮሉአቸው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ጨካኞች የሆኑትም አሠሪዎች ቀድሞ ገለባ እየሰጡአቸው ይሠሩት የነበረውን ያኽል ጡብ ቈጥረው እንዲያስረክቡ ያስገድዱአቸው ጀመር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አስገባሪዎቹም፥ “ገለባ ትቀበሉበት እንደ ነበረ ጊዜ የቀን ሥራችሁን ጨርሱ፤” እያሉ አስቸኮሉአቸው።

Ver Capítulo



ዘፀአት 5:13
7 Referencias Cruzadas  

እንደ ተጻ​ፈ​ውም የዳስ በዓል አደ​ረጉ፤ እንደ ሥር​ዐ​ቱም ለየ​ዕ​ለቱ የተ​ገ​ባ​ውን የየ​ዕ​ለ​ቱን የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በቍ​ጥር አቀ​ረቡ።


በከ​ተ​ማው ሕዝብ ውካታ ይዘ​ብ​ታል፤ የሚ​ያ​ስ​ፈ​ራ​ው​ንም ጩኸት አይ​ሰ​ማም።


በብ​ርቱ ሥራም ያስ​ጨ​ን​ቋ​ቸው ዘንድ የሠ​ራ​ተ​ኞች አለ​ቆ​ችን ሾመ​ባ​ቸው፤ ለፈ​ር​ዖ​ንም ፌቶ​ምን፥ ራም​ሴ​ንና የፀ​ሐይ ከተማ የም​ት​ባል ዖንን ጽኑ ከተ​ሞች አድ​ር​ገው ሠሩ።


እና​ንተ ሂዱ፤ ከም​ታ​ገ​ኙ​በ​ትም ስፍራ ገለባ ሰብ​ስቡ፤ ከም​ት​ሠ​ሩት ጡብ ግን ምንም አይ​ጐ​ድ​ልም” አሉ​አ​ቸው።


ሕዝ​ቡም ሁሉ ስለ ገለባ እብቅ ሊሰ​በ​ስቡ በግ​ብፅ ምድር ሁሉ ተበ​ተኑ።


የፈ​ር​ዖ​ንም ሹሞች፥ “ቀድሞ ታደ​ር​ጉት እንደ ነበ​ራ​ችሁ እንደ ትና​ን​ት​ና​ውና እንደ ትና​ን​ትና በስ​ቲ​ያው የተ​ቈ​ጠ​ረ​ውን ጡብ ዛሬስ ስለ​ምን አት​ጨ​ር​ሱም?” እያሉ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ላይ የተ​ሾ​ሙ​ትን አለ​ቆች ይገ​ርፉ ነበር።


ፈር​ዖ​ንም በዚያ ቀን የሕ​ዝ​ቡን አሠ​ሪ​ዎ​ችና ጸሓ​ፊ​ዎች እን​ዲህ ሲል አዘዘ፦