በብርቱ ሥራም ያስጨንቋቸው ዘንድ የሠራተኞች አለቆችን ሾመባቸው፤ ለፈርዖንም ፌቶምን፥ ራምሴንና የፀሐይ ከተማ የምትባል ዖንን ጽኑ ከተሞች አድርገው ሠሩ።
ዘፀአት 5:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሕዝቡም አሠሪዎችና ጸሓፊዎች ወጡ፤ ሕዝቡንም፥ “ፈርዖን እንዲህ ይላል፦ እንግዲህ ገለባ አይሰጣችሁም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም የባሪያ ተቈጣጣሪዎቹና አለቆቹ ወጥተው ለሕዝቡ፣ “ፈርዖን የሚለው ይህ ነው፤ ‘ከእንግዲህ ጭድ አልሰጣችሁም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሕዝቡ አስገባሪዎችና ሹማምንቶቹም ወጡ፥ ሕዝቡንም አሉት፦ “ፈርዖን እንዲህ ይላል፦ ‘ገለባ አልሰጣችሁም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጨካኞች የሆኑት ግብጻውያን አሠሪዎችና የእስራኤላውያን ሠራተኞች አለቆች ሄደው ለእስራኤል ሕዝብ እንዲህ አሉ፤ “ንጉሡ ከእንግዲህ ወዲህ ገለባ እንዳይሰጣችሁ አዞአል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሕዝቡም አስገባሪዎች ሹማምቶቹም ወጡ፤ ሕዝቡንም፥ “ፈርዖን እንዲህ ይላል፦ ‘ገለባ አልሰጣችሁም። |
በብርቱ ሥራም ያስጨንቋቸው ዘንድ የሠራተኞች አለቆችን ሾመባቸው፤ ለፈርዖንም ፌቶምን፥ ራምሴንና የፀሐይ ከተማ የምትባል ዖንን ጽኑ ከተሞች አድርገው ሠሩ።
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “በግብፅ ያለውን የሕዝቤን መከራ በእውነት አየሁ፦ ከአሠሪዎቻቸውም የተነሣ ጩኸታቸውን ሰማሁ፤ ሥቃያቸውንም ዐውቄአለሁ፤
ተባትና እንስት አንበሳ፥ እፉኝትም፥ ነዘር እባብም፥ በሚወጡባት በመከራና በጭንቀት ምድር በኩል ብልጽግናቸውን በአህዮች ጫንቃ ላይ፥ መዛግብቶቻቸውንም በግመሎች ሻኛ ላይ እየጫኑ ወደማይጠቅሙአቸው ሕዝብ ይሄዳሉ።