የሁለቱንም ቋዶች ጫፎች በሁለቱ ፈርጦች ውስጥ አግብተህ በልብሰ መትከፉ ጫንቃዎች ላይ በስተፊት በመጋጠሚያቸው ታደርጋቸዋለህ።
ዘፀአት 39:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁለቱ ወገን እንዲጋጠሙ፥ በሁለት ጫንቃዎች ላይ የሚጋጠም ልብሰ መትከፍ ሠሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለኤፉዱ ከሁለቱ ጐኖቹ ጋራ ተያይዘው ያሉትን የትከሻ ንጣዮችን ሠሩ፤ ይኸውም ማያያዝ እንዲቻል ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲጋጠም በሁለቱ ትከሻዎች ላይ መጋጠሚያ ሠሩለት፥ በሁለቱ ጫፎች እንዲጋጠም አደረጉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለኤፉዱም ማንገቻ በትከሻ ላይ የሚወርዱ ሁለት ጥብጣቦች ሠርተው ኤፉዱ እንዲጠብቅ በጐንና በጐኑ አያያዙአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁለቱ ወገን እንዲጋጠም በሁለቱ ጫንቃዎች ላይ የሚጋጠም ልብስ አደረጉት። |
የሁለቱንም ቋዶች ጫፎች በሁለቱ ፈርጦች ውስጥ አግብተህ በልብሰ መትከፉ ጫንቃዎች ላይ በስተፊት በመጋጠሚያቸው ታደርጋቸዋለህ።
ወርቁንም ቀጥቅጠው እንደ ቅጠል ስስ አደረጉት፤ እንደ ፈትልም ቈረጡት። ብልህ ሠራተኛም እንደሚሠራ ሰማያዊ፥ ሐምራዊም፥ ቀይ ግምጃም፥ የተፈተለም ጥሩ በፍታ፥ ከእርሱ ጠለፉ።
እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው እርስዋን ከወርቅ፥ ከሰማያዊና ከሐምራዊ፥ ከቀይ ግምጃም፥ ከተፈተለ ከጥሩ በፍታም እንደ ሠሩ የልብሰ መትከፉን ቋድ ሠሩ።