ለመሠዊያውም እንደ መረብ ሆኖ የተሠራ የናስ መከታ አድርግለት፤ ለመከታውም አራት የናስ ቀለበት በአራት ማዕዘኑ አድርግለት።
ዘፀአት 38:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደ መረብ ሆኖም የተሠራ የናስ መከታ ለመሠዊያው አደረገ፤ መከታውም እስከ መሠዊያው እኩሌታ ይደርስ ዘንድ በመሠዊያው በሚዞረው በደረጃው ታች አደረገው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለመሠዊያውም ከጠርዝ በታች ሆኖ ከመሠዊያው ግማሽ ቁመት ላይ የሚሆን የንሓስ ፍርግርግ ማንደጃ ሠሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለመሠዊያውም መረብ የሚመስል የነሐስ መከታ ከጠርዙ በታች እስከ መሠዊያው ግማሽ ድረስ ሠራለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መረብ የሚመስል የነሐስ መከላከያ ሠራ፤ እርሱንም እስከ መሠዊያ ግማሽ ቁመት እንዲደርስ አድርጎ በመሠዊያው ክፈፍ ሥር አኖረው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደ መረብ ሆኖም የተሠራ የናስ መከታ ለመሠዊያ አደረገ፤ መከታውም እስከ መሠዊያው እኩሌታ ይደርስ ዘንድ በመሠዊያው በሚዞረው በደረጃው ታች አደረገው። |
ለመሠዊያውም እንደ መረብ ሆኖ የተሠራ የናስ መከታ አድርግለት፤ ለመከታውም አራት የናስ ቀለበት በአራት ማዕዘኑ አድርግለት።
የመሠዊያውንም ዕቃ ሁሉ፥ ምንቸቶቹንም፥ መጫሪያዎቹንም፥ ድስቶቹንም፥ ሜንጦዎቹንም፥ የእሳት ማንደጃዎቹንም አደረገ፤ ዕቃውንም ሁሉ ከናስ አደረገ።