ለመጋረጃውም አምስት ምሰሶዎች ከማይነቅዝ ዕንጨት አድርግ፤ በወርቅም ለብጣቸው፤ ኩላቦቻቸውም ከወርቅ የተሠሩ ይሁኑ፤ አምስትም የናስ እግሮች አድርግላቸው።
ዘፀአት 38:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእርሱም የምስክሩን ድንኳን ደጃፍ እግሮች፥ የናሱንም መሠዊያ፥ ለእርሱም የሆነውን የናሱን መከታ፥ የመሠዊያውንም ዕቃ ሁሉ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለመገናኛው ድንኳን መግቢያ ለናስ መሠዊያው ከናስ መጫሪያው፣ ለዕቃዎቹም ሁሉ መቆሚያዎቹን ለመሥራት አገልግሎት ላይ አውለውት ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእርሱም የመገናኛውን ድንኳን መግቢያ እግሮች፥ የነሐሱን መሠዊያ፥ ለእርሱም የሚያገለግለውን የነሐሱን መከታ፥ የመሠዊያውንም ዕቃ ሁሉ ሠራ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ መገናኛው ድንኳን መግቢያ የሆነው ደጃፍ የሚቆምባቸውን እግሮች፥ ከነሐስ መከላከያው ጋር የነሐስ መሠዊያውን፥ ለመሠዊያው መገልገያ የሆኑትን ዕቃዎች በሙሉ ከዚህ ነሐስ ሠራ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእርሱም የመገናኛውን ድንኳን ደጃፍ እግሮች፥ የናሱንም መሠዊያ፥ ለእርሱም የሆነውን የናሱን መከታ፥ የመሠዊያውንም ዕቃ ሁሉ፥ |
ለመጋረጃውም አምስት ምሰሶዎች ከማይነቅዝ ዕንጨት አድርግ፤ በወርቅም ለብጣቸው፤ ኩላቦቻቸውም ከወርቅ የተሠሩ ይሁኑ፤ አምስትም የናስ እግሮች አድርግላቸው።
ለመሠዊያውም እንደ መረብ ሆኖ የተሠራ የናስ መከታ አድርግለት፤ ለመከታውም አራት የናስ ቀለበት በአራት ማዕዘኑ አድርግለት።
በአደባባዩ ዙሪያ ያሉትን እግሮች፥ የአደባባዩንም ደጃፍ እግሮች፥ የድንኳኑንም ካስማዎች ሁሉ፥ በአደባባዩ ዙሪያም ያሉትን ካስማዎች ሁሉ አደረገ።