ዘፀአት 37:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መቅረዙንም፥ ዕቃውንም ሁሉ ከአንድ መክሊት ጥሩ ወርቅ አደረገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መቅረዙንና ዕቃዎቹን ሁሉ ከአንድ መክሊት ንጹሕ ወርቅ ሠሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መቅረዙንና ዕቃዎቹን ሁሉ ከአንድ መክሊት ንጹሕ ወርቅ ሠራ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መቅረዙንና የእርሱን መገልገያ ዕቃዎች ሁሉ ለመሥራት የፈጀበት የወርቅ መጠን ሠላሳ አምስት ኪሎ ግራም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መቅረዙንም ዕቃውንም ሁሉ ከአንድ መክሊት ጥሩ ወርቅ አደረገ። |
የዕጣን መሠዊያንም ከማይነቅዝ ዕንጨት ሠራ፤ ርዝመቱ አንድ ክንድ፥ ስፋቱ አንድ ክንድ፤ አራት ማዕዘን ነበር፤ ከፍታውም ሁለት ክንድ ነበር፤ ቀንዶቹም ከእርሱ ጋር በአንድነት የተሠሩ ነበሩ።