እያንዳንዱም መጋረጃ ርዝመቱ ሠላሳ ክንድ፥ እያንዳንዱም መጋረጃ ወርዱ አራት ክንድ ነበረ፤ የእያንዳንዱም መጋረጃ መጠኑ ትክክል ነበረ።
ዘፀአት 36:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምስቱንም መጋረጃዎች እርስ በርሳቸው አንድ አደረጉ፤ ስድስቱንም መጋረጃዎች አንድ አድርገው አጋጠሙአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐምስቱን መጋረጃዎች በአንድ በኩል፣ ሌሎቹን ስድስት መጋረጃዎች ደግሞ በሌላ በኩል አንድ ላይ አያያዟቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አምስቱን መጋረጃዎች አንድ ላይ ለብቻ፥ ስድስቱንም መጋረጃዎች አንድ ላይ ለብቻ አድርጎ አጋጠማቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምስቱን በአንድ በኩል፥ ስድስቱንም በሌላ በኩል በማድረግ አገጣጥመው ሰፉአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምስቱንም መጋረጆች እርስ በርሳቸው አንድ አድርገው፥ ስድስቱንም መጋረጆች አንድ አድርገው አጋጠሙአቸው። |
እያንዳንዱም መጋረጃ ርዝመቱ ሠላሳ ክንድ፥ እያንዳንዱም መጋረጃ ወርዱ አራት ክንድ ነበረ፤ የእያንዳንዱም መጋረጃ መጠኑ ትክክል ነበረ።
ከተጋጠሙትም መጋረጃዎች በአንደኛው መጋረጃ ጠርዝ ላይ አምሳ ቀለበቶችን አደረጉ፤ እንዲሁም በሁለተኛው መጋረጃ ጠርዝ በሚጋጠሙበት በኩል አምሳ ቀለበቶችን አደረጉ።