በቅርጽ ሠራተኛ ሥራ እንደ ማኅተም ቅርጽ አድርገህ የእስራኤልን ልጆች ስሞች በሁለት ድንጋዮች ቅረጽ፤ በወርቅም ፈርጥ አድርግ።
ዘፀአት 28:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሁለቱንም ቋዶች ጫፎች በሁለቱ ፈርጦች ውስጥ አግብተህ በልብሰ መትከፉ ጫንቃዎች ላይ በስተፊት በመጋጠሚያቸው ታደርጋቸዋለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሌሎቹን የጕንጕን ጫፎች በፊት ላይ ካለው ኤፉድ በትከሻው ላይ ካሉት ንጣዮች ጋራ በማጋጠም ከሁለቱ የወርቅ ፈርጦች ጋራ አያይዛቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሁለቱን ድሪዎች ጫፎች በሁለቱ ፈርጦች ውስጥ አግብተህ በኤፉዱ ትከሻ በፊት ለፊት ታደርጋቸዋለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሌላ በኩል ያሉትንም የሁለቱን ድሪዎች ጫፎች ከሁለቱ ፈርጦች ጋር አገናኛቸው፤ በዚህም ዐይነት ከፊት ለፊት በኩል በትከሻ ላይ ከሚወርዱት ከኤፉዱ ማንገቻዎች ጋር ታያይዛቸዋለህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሁለቱንም ድሪዎች ጫፎች በሁለቱ ፈርጦች ውስጥ አግብተህ በኤፉዱ ጫንቃዎች በፊታቸው ታደርጋቸዋለህ። |
በቅርጽ ሠራተኛ ሥራ እንደ ማኅተም ቅርጽ አድርገህ የእስራኤልን ልጆች ስሞች በሁለት ድንጋዮች ቅረጽ፤ በወርቅም ፈርጥ አድርግ።
ሁለት ቋዶችንም ከጥሩ ወርቅ እንደ ተጐነጐነ ገመድ አድርገህ ሥራ፤ የተጐነጐኑትንም ቋዶች በፈርጦቹ ላይ አንጠልጥል።
የተጐነጐኑትንም ሁለቱን የወርቅ ቋዶች በልብሰ እንግድዓው በሁለት ወገኖች ወዳሉት ወደ ሁለት ቀለበቶች ታገባቸዋለህ።
ሁለት የወርቅ ቀለበቶችንም ሥራ፤ እነርሱንም ልብሰ መትከፉ በውስጥ በሚያልፍበት በከንፈሩ በኩል በሁለቱ የልብሰ እንግድዓ ጫፎች ላይ ታኖራቸዋለህ።