ዘፀአት 28:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለልብሰ እንግድዓውም ሁለት የወርቅ ቀለበቶች ሥራ፤ ሁለቱንም ቀለበቶች በልብሰ እንግድዓው በሁለቱ ወገን አድርጋቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለርሱም ሁለት የወርቅ ቀለበቶች አብጅተህ ከደረት ኪሱ ሁለት ጐኖች ጋራ አያይዘው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለደረት ኪሱም ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን ሥራ፥ ሁለቱንም ቀለበቶች በደረት ኪሱ በሁለቱ ጫፎች አድርጋቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁለት የወርቅ ቀለበቶች ሠርተህ በደረት ኪሱ ከላይኛው ማእዘን በኩል እንዲጋጠሙ አድርግ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለደረቱ ኪስም ሁለት የወርቅ ቀለበቶች ሥራ፥ ሁለቱንም ቀለበቶች በደረቱ ኪስ በሁለቱ ወገን አድርጋቸው። |
የተጐነጐኑትንም ሁለቱን የወርቅ ቋዶች በልብሰ እንግድዓው በሁለት ወገኖች ወዳሉት ወደ ሁለት ቀለበቶች ታገባቸዋለህ።