ዘፀአት 28:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አራተኛውም ተራ ወርቃማ ድንጋይ፥ ቢረሌ፥ ሶም በየተራቸው በወርቅ የተለበጡና የታሠሩ ይሆናሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአራተኛውም ረድፍ ቢረሌ፣ መረግድና ኢያሰጲድ አድርግበት፤ በወርቅ ፈርጥም ክፈፋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአራተኛው ረድፍ ቢረሌ፥ መረግድ፥ ኢያስጲድ፤ በወርቅ ፈርጥ ይቀመጣሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአራተኛው ረድፍ ቢረሌ፥ መረግድና ኢያስጲድ በወርቅ ፈርጥ ላይ ይቀመጣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአራተኛውም ተራ ቢረሌ፥ መረግድ፥ ኢያስጲድ በወርቅ ፈርጥ ይደረጋሉ። |
የዕንቍም ድንጋዮች እንደ እስራኤል ልጆች ስሞች ዐሥራ ሁለት ይሆናሉ፤ በየስማቸውም ማኅተም አቀራረጽ ይቀረጹ፤ ስለ ዐሥራ ሁለቱ ነገዶችም ይሁኑ።
እጆቹ የተርሴስ ፈርጥ እንዳለባቸው እንደ ለዘቡ የወርቅ ቀለበቶች ናቸው፤ ሆዱ በሰንፔር ዕንቍ እንዳጌጠ እንደ ዝሆን ጥርስ ነው፥
የመንኰራኵሩም መልክ እንደ ቢረሌ ነበረ፤ አራቱም አንድ አምሳያ ነበሩ፤ ሥራቸውም በመንኰራኵር ውስጥ እንዳለ መንኰራኵር ነበረ።
እኔም አየሁ፤ እነሆም በኪሩቤል አጠገብ አራት መንኰራኵሮች ነበሩ፤ አንዱ መንኰራኵር በአንዱ ኪሩብ፥ አንዱ መንኰራኵር በአንዱ ኪሩብ አጠገብ ነበረ። የመንኰራኵሮቹም መልክ እንደ ቢረሌ ድንጋይ ነበረ።