በቅርጽ ሠራተኛ ሥራ እንደ ማኅተም ቅርጽ አድርገህ የእስራኤልን ልጆች ስሞች በሁለት ድንጋዮች ቅረጽ፤ በወርቅም ፈርጥ አድርግ።
ዘፀአት 28:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአራት ተራ የሆነ የዕንቍ ፈርጥ አድርግበት፤ የድንጋዮቹም ተራ ሰርድዮን፥ ጳዝዮን፥ መረግድ ነው፤ ይህም መጀመሪያው ተራ ነው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም በላዩ ላይ በአራት ረድፍ የከበሩ ድንጋዮች አድርግበት፤ በመጀመሪያው ረድፍ ሰርድዮን፣ ቶጳዝዮን፣ የሚያበረቀርቅ ዕንቍ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አራት ረድፍ የሆነ የዕንቁ ፈርጥ አድርግበት፤ በመጀመሪያው ረድፍ ሰርድዮን፥ ቶጳዝዮንና የሚያብረቀርቅ ዕንቁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አራት ረድፍ የሆነ የዕንቊ ፈርጥ አድርግበት፤ በመጀመሪያው ረድፍ ሰርድዮን፥ ቶጳዝዮንና፥ የሚያብረቀርቅ ዕንቊ፥ 18 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአራት ተራ የሆነ የዕንቁ ፍርጥ አድርግበት፤ በፊተኛው ተራ ሰርድዮን፥ ቶጳዝዮን፥ የሚያብረቀርቅ ዕንቁ፤ |
በቅርጽ ሠራተኛ ሥራ እንደ ማኅተም ቅርጽ አድርገህ የእስራኤልን ልጆች ስሞች በሁለት ድንጋዮች ቅረጽ፤ በወርቅም ፈርጥ አድርግ።
ዛይ። ቅዱሳኖችዋ ከበረድ ይልቅ ነጡ፤ ከወተትም ይልቅ ነጡ፤ በመውጣታቸውም ሰንፔር ከሚባል ዕንቍ ይልቅ ፈጽመው ቀሉ።
በእግዚአብሔር ገነት በዔድን ነበርህ፤ የከበረ ዕንቍስ ሁሉ፥ ሰርድዮን፥ ቶጳዝዮን፥ አልማዝ፥ ቢረሌ፥ መረግድ፥ ኢያሰጲድ፥ ሰንፔር፥ በሉር፥ የሚያብረቀርቅ ዕንቍ፥ ወርቅም ልብስህ ነበረ፤ የከበሮህና የእንቢልታህ ሥራ በአንተ ዘንድ ነበረ፤ በተፈጠርህበትም ቀን ተዘጋጅተው ነበር።
እኔ በምሠራበት ቀን እነርሱ የእኔ ገንዘብ ይሆናሉ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ ሰውም የሚያገለግለውን ልጁን እንደሚምር፥ እንዲሁ እምራቸዋለሁ።