“ብልህ ሠራተኛም እንደሚሠራ የፍርዱን ልብሰ እንግድዓ ሥራው፤ እንደ ልብሰ መትከፍም አሠራር ሥራው፤ ከወርቅና ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊም፥ ከቀይም ግምጃ፥ ከጥሩ በፍታም ሥራው።
ዘፀአት 28:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ርዝመቱ ስንዝር ስፋቱም ስንዝር፥ ሆኖ አራት ማዕዘን ድርብ ይሁን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ርዝመቱ አንድ ስንዝር፣ ወርዱም አንድ ስንዝር ሆኖ ባለአራት ማእዘንና በድርቡ የታጠፈ ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ርዝመቱ ስንዝር ስፋቱም ስንዝር ሆኖ አራት መዕዘንና ድርብ ይሁን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ርዝመቱ ኻያ ሁለት ሳንቲ ሜትር የጐኑም ስፋት ኻያ ሁለት ሳንቲ ሜትር ሆኖ ታጥፎ የተደረበ ትክክል አራት ማእዘን ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ርዝመቱ ስንዝር ስፋቱም ስንዝር ሆኖ ትክክልና ድርብ ይሆናል። |
“ብልህ ሠራተኛም እንደሚሠራ የፍርዱን ልብሰ እንግድዓ ሥራው፤ እንደ ልብሰ መትከፍም አሠራር ሥራው፤ ከወርቅና ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊም፥ ከቀይም ግምጃ፥ ከጥሩ በፍታም ሥራው።
በአራት ተራ የሆነ የዕንቍ ፈርጥ አድርግበት፤ የድንጋዮቹም ተራ ሰርድዮን፥ ጳዝዮን፥ መረግድ ነው፤ ይህም መጀመሪያው ተራ ነው፤